ዘኍል 34:18 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ምድሪቱንም ርስት አድርገው ለመከፋፈል ከየነገዱ አንድ አንድ አለቃ ትወስዳላችሁ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ምድሪቱን በማከፋፈሉ እንዲረዱም ከየነገዱ አንዳንድ መሪ ውሰዱ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ምድሪቱን ለማከፋፈል ይረዱ ዘንድ ከየነገዱ አንድ አንድ መሪ ውሰድ።” የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ምድሪቱንም ርስት አድርገው የሚያካፍሏቸው ከየነገዱ አንድ አንድ አለቃ ይወስዳሉ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ምድሪቱንም ርስት አድርገው ይከፍሉ ዘንድ ከየነገዱ አንድ አንድ አለቃ ትወስዳላችሁ። |
ካህኑ አልዓዛር፥ የነዌም ልጅ ኢያሱ፥ የእስራኤልም ልጆች ነገዶች የአባቶች አለቆች በጌታ ፊት በሴሎ በመገናኛው ድንኳን ደጃፍ አጠገብ በዕጣ ያከፋፈሉት ርስት ይህ ነው። ምድሪቱንም አከፋፍለው ጨረሱ።