ዘኍል 31:26 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) “አንተና ካህኑ አልዓዛር የማኅበሩም አባቶች አለቆች የተማረኩትን ሰውና እንስሳ ቁጠሩ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም “አንተ፣ ካህኑ አልዓዛርና በማኅበረ ሰቡ ውስጥ ያሉት የየቤተ ሰቡ አለቆች ሆናችሁ የተማረከውን ሕዝብና እንስሳት ሁሉ ቍጠሩ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም “አንተና አልዓዛር ከቀሩት የማኅበሩ መሪዎች ጋር በመሆን እስረኞችንና እንስሶችን ጭምር በምርኮ የተገኘውን ማንኛውንም ነገር ቊጠሩ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) “አንተና ካህኑ አልዓዛር፥ የማኅበሩም አባቶች አለቆች የተማረኩትን ሰውና እንስሳ ቍጠሩ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) አንተና ካህኑ አልዓዛር የማኅበሩም አባቶች አለቆች የተማረኩትን ሰውና እንስሳ ቍጠሩ። |