ዘኍል 27:23 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ጌታም በሙሴ እንደ ተናገረ፥ እጁን በእርሱ ላይ ጫነበት፥ አዘዘውም። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከዚያም እግዚአብሔር በሙሴ አማካይነት ባዘዘው መሠረት እጁን በራሱ ላይ ጭኖ ሾመው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እግዚአብሔር ባዘዘው መሠረት ሙሴ እጆቹን በኢያሱ ራስ ላይ ጭኖ ከዚያ በኋላ የእርሱ ተተኪ መሆኑን በግልጥ አስታወቀ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እግዚአብሔርም ሙሴን እንደ አዘዘው፥ እጁን በላዩ ጫነበትና፥ ሾመው፤ አዘዘውም። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እግዚአብሔርም በሙሴ እንደ ተናገረ፥ እጁን በላዩ ጫነበት፥ አዘዘውም። |
ኢያሱንም ያንጊዜ አዘዝኩት፦ “ጌታ አምላካችሁ በእነዚህ በሁለቱ ነገሥታት ያደረገውን ሁሉ ዐይኖችህ አይተዋል፥ እንዲሁ ሁሉ በምታልፍባቸው መንግሥታት ላይ ጌታ ያደርጋል።
ጌታም ለነዌ ልጅ ለኢያሱ፥ “በርታ፤ ደፋር ሁን፤ የእስራኤልን ልጆች በመሐላ ቃል ወደ ገባሁላቸው ምድር ታስገ ባቸዋለህና፤ እኔም ከአንተ ጋር እሆናለሁ” በማለት ትእዛዝ ሰጠው።