La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




ዘኍል 27:12 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

ጌታም ሙሴን እንዲህ አለው፦ “ወደዚህ ወደ ዓባሪም ተራራ ውጣ፥ ለእስራኤልም ልጆች የሰጠኋትን ምድር እይ፤

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

ከዚያም እግዚአብሔር ሙሴን እንዲህ አለው፤ “በዓባሪም ሸንተረር ላይ ወዳለው ወደዚህ ተራራ ውጣና ለእስራኤላውያን የሰጠኋቸውን ምድር እይ።

Ver Capítulo

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

እግዚአብሔር ሙሴን እንዲህ አለው፤ “ወደ ዐባሪም ተራራ ወጥተህ ለእስራኤላውያን ልሰጣቸው ያቀድኩትን ምድር ሁሉ እይ፤

Ver Capítulo

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ሙሴን አለው፥ “ወደ​ዚህ በና​ባው አሻ​ገር ወዳ​ለው ተራራ ውጣ፤ ለእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ልጆች ይገ​ዙ​አት ዘንድ እኔ የም​ሰ​ጣ​ቸ​ውን የከ​ነ​ዓ​ንን ምድር እያት፤

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

እግዚአብሔርም ሙሴን አለው፦ ወደዚህ ወደ ዓባሪም ተራራ ውጣ፥ ለእስራኤልም ልጆች የሰጠኋትን ምድር እይ፤

Ver Capítulo



ዘኍል 27:12
7 Referencias Cruzadas  

በእንግድነት የምትኖርባትን ምድር፥ የከነዓን ምድር ሁሉ፥ ለዘለዓለም ግዛት ይሆንህ ዘንድ ለአንተና ከአንተ በኋላ ለዘርህ እሰጣለሁ፥ አምላክም እሆናቸዋለሁ።”


“ውሽሞችሽ ሁሉ ጠፍተዋልና ወደ ሊባኖስ ወጥተሽ ጩኺ፤ በባሳን ላይ ድምፅሽን ከፍ አድርጊ፤ ከዓባሪምም ሆነሽ ጩኺ።


ጌታ ሙሴን፥ “እነሆ የምትሞትበት ቀን ቀርቧል፤ ትእዛዝ እንድሰጠው ኢያሱን ጥራውና ወደ መገናኛው ድንኳን ቅረቡ።” ሙሴና ኢያሱም ሄዱ፤ ወደ መገናኛው ድንኳንም ቀረቡ።