La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




ዘኍል 26:9 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

የኤልያብም ልጆች፤ ነሙኤል፥ ዳታን፥ አቤሮን ናቸው፤ እነዚህ ዳታንና አቤሮን ከማኅበሩ የተመረጡ ነበሩ፤ ቆሬን ከተከተሉት ሰዎች ጋር በመሆን በጌታ ላይ ባመፁ ጊዜ ሙሴንና አሮንን የተገዳደሩ ነበሩ፤

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

የኤልያብ ልጆች ደግሞ፣ ነሙኤል ዳታንና አቤሮን ነበሩ። እነዚሁ ዳታንና አቤሮን በሙሴና በአሮን ላይ ያመፁ የማኅበሩ ሹማምት ሲሆኑ፣ ቆሬና ተከታዮቹ በእግዚአብሔር ላይ ባመፁ ጊዜ እነርሱም በነገሩ ነበሩበት።

Ver Capítulo

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

የኤሊአብ ልጆች ነሙኤል፥ ዳታንና አቤሮን ነበሩ፤ ዳታንና አቤሮንም በማኅበሩ ተመርጠው የነበሩት ሲሆኑ እነርሱም ከቆሬና ከተከታዮቹ ጋር ተባብረው በእግዚአብሔር ላይ ባመፁ ጊዜ ሙሴንና አሮንን የተፈታተኑአቸው ናቸው።

Ver Capítulo

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

የኤ​ል​ያ​ብም ልጆች፥ ናሙ​ኤል፥ ዳታን፥ አቤ​ሮን፤ እነ​ዚ​ህም ከማ​ኅ​በሩ የተ​መ​ረጡ ነበሩ፤ ከቆሬ ወገን ጋር በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ላይ ባመፁ ጊዜ ሙሴ​ንና አሮ​ንን ተጣሉ፤

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

የኤልያብም ልጆች፤ ነሙኤል፥ ዳታን፥ አቤሮን፤ እነዚህ ዳታንና አቤሮን ከማኅበሩ የተመረጡ ነበሩ፤ ከቆሬ ወገን ጋር በእግዚአብሔር ላይ ባመፁ ጊዜ ሙሴንና አሮንን ተጣሉ፤

Ver Capítulo



ዘኍል 26:9
5 Referencias Cruzadas  

ምድርም ተከፈተች ዳታንንም ዋጠችው፥ የአቤሮንንም ወገን ደፈነች፥


ከማኅበሩ የተመረጡ የእስራኤል የወገኖቻቸው አውራዎች፥ የአባቶቻቸው ነገድ አለቆች እነዚህ ነበሩ።


የፈሉስም ልጆች፤ ኤልያብ።


ወዮላቸው! በቃየል መንገድ ሄደዋልና፥ ለደመወዝ ብለው ለበለዓም ስሕተት ራሳቸውን አሳልፈው ሰጥተዋል፥ በቆሬም ዓመጽ ጠፍተዋል።