La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




ዘኍል 26:5 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

የእስራኤል በኩር ሮቤል፤ የሮቤልም ልጆች እነዚህ ናቸው፤ ከሄኖኅ የሄኖኀውያን ወገን፥ ከፈሉስ የፈሉሳውያን ወገን፥

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

የእስራኤል የበኵር ልጅ የሆነው የሮቤል ዘሮች እነዚህ ነበሩ፤ በሄኖኅ በኩል፣ የሄኖኀውያን ጐሣ፤ በፈሉስ በኩል፣ የፈሉሳውያን ጐሣ፤

Ver Capítulo

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

የያዕቆብ የበኲር ልጅ የሮቤል ነገድ ተወላጆች ሐኖክ፥ ፋሉስ፥

Ver Capítulo

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

የእ​ስ​ራ​ኤል በኵር ሮቤል፤ የሮ​ቤል ልጆች፤ ከሄ​ኖኅ የሄ​ኖ​ኃ​ው​ያን ወገን፤ ከፈ​ሉስ የፈ​ሉ​ሳ​ው​ያን ወገን።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

የእስራኤል በኵር ሮቤል፤ የሮቤል ልጆች፤ ከሄኖኅ የሄኖኀውያን ወገን፥ ከፈሉስ የፈሉሳውያን ወገን፥

Ver Capítulo



ዘኍል 26:5
11 Referencias Cruzadas  

ልያም ፀነሰች፥ ወንድ ልጅንም ወለደች፥ ስሙንም ሮቤል ብላ ጠራችው፥ እግዚአብሔር መከራዬን አይቶአልና፥ እንግዲህም ወዲህ ባሌ ይወድደኛል ብላለችና።


እስራኤልም በዚያች አገር በተቀመጠ ጊዜ ሮቤል ሄደ የአባቱንም ቁባት ባላን ተገናኛት፥ እስራኤልም ሰማ። የያዕቆብም ልጆች ዐሥራ ሁለት ናቸው፥


የልያ ልጆች፥ የያዕቆብ በኩር ልጅ ሮቤል፥ ስምዖን፥ ሌዊ፥ ይሁዳ፥ ይሳኮር፥ ዛብሎን፥


የእስራኤልም በኩር የሮቤል ልጆች እነዚህ ናቸው። እርሱ የበኩር ልጅ ነበረ፤ ነገር ግን የአባቱን ምንጣፍ ስላረከሰ ብኩርናው ለእስራኤል ልጅ ለዮሴፍ ልጆች ተሰጠ፤ ትውልዱ ግን ከብኩርናው ጋር አልተቈጠረም።


የእስራኤል በኩር የሮቤል ልጆች፤ ሄኖኅ፥ ፈሉሶ፥ አስሮን፥ ከርሚ ነበሩ።


የአባቶቻቸው ቤት አለቆች እነዚህ ናቸው። የእስራኤል የበኩር ልጅ የሮቤል ልጆች ሐኖክ፥ ፋሉ፥ ሔፅሮንና ካርሚ፤ እነዚህ የሮቤል ወገኖች ናቸው።


“የእስራኤል በኩር የሮቤል ልጆች በየትውልዳቸው፥ በየወገኖቻቸው፥ በየአባቶቻቸው ቤቶች፥ እንደየስማቸው ቍጥር፥ አንድ በአንድ፥ ዕድሜው ሀያ ዓመት የሆነውንና ከዚያም በላይ ያለውን ወንድ ሁሉ፥ ወደ ጦርነት የሚወጣው ሁሉ፥


ጌታ ሙሴን እንዳዘዘው “ዕድሜው ሀያ ዓመት የሆነውንና ከዚያም በላይ ያለውን ሕዝብ ቁጠሩ።” ከግብጽም ምድር የወጡት የእስራኤል ልጆች እነዚህ ነበሩ፦


ከአስሮን የአስሮናውያን ወገን፥ ከከርሚ የከርማውያን ወገን።