La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




ዘኍል 24:3 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

እርሱም ምሳሌውን ይመስል ጀመር፥ እንዲህም አለ፦ “የቢዖር ልጅ በለዓም እንዲህ ይላል፥ ዐይኖቹ የተከፈቱለት ሰው እንዲህ ይላል፤

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

ንግሩንም እንዲህ ሲል ጀመረ፤ “የዚያ ዐይኑ የተከፈተለት፣ የቢዖር ልጅ የበለዓም ንግር፣

Ver Capítulo

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

እንዲህ ሲል ትንቢት ተናገረ፤ “የቢዖር ልጅ በለዓም የሚናገረው የትንቢት ቃል ይህ ነው፤ እርሱም ሁሉን ነገር በግልጥ ማየት የሚችልና፥

Ver Capítulo

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

በም​ሳ​ሌም ይና​ገር ጀመር፤ እን​ዲ​ህም አለ፥ “የቢ​ዖር ልጅ በለ​ዓም እን​ዲህ ይላል፥ በት​ክ​ክል የሚ​ያይ ሰው እን​ዲህ ይላል፤

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

ምሳሌውን ይመስል ጀመር፥ እንዲህም አለ፦ የቢዖር ልጅ በለዓም እንዲህ ይላል፥ ዓይኖቹ የተከፈቱለት ሰው እንዲህ ይላል፤

Ver Capítulo



ዘኍል 24:3
9 Referencias Cruzadas  

ሚክያስም “መላው የእስራኤል ሠራዊት ጠባቂ እንደሌላቸው በጎች በኮረብታዎች ላይ ተበታትነው አያለሁ፤ ጌታም ‘እነዚህ ሰዎች መሪ የላቸውም፤ ስለዚህ ወደየቤታቸው በሰላም ይመለሱ ብሏል’ ሲል መለሰለት።”


ሚክያስም ንግግሩን በመቀጠል እንዲህ አለ፤ “እንግዲህ ጌታ የሚለውን ስማ! ጌታ በሰማይ ባለው ዙፋኑ ላይ ተቀምጦ፥ መላእክቱም ሁሉ በቀኝና በግራው ቆመው አየሁ፤


ኢዮብም ንግግሩን ቀጠለ፤ እንዲህም አለ፦


ጌታም የበለዓምን ዐይኖች ከፈተ፤ የጌታም መልአክ በመንገድ ላይ ቆሞ የተምዘዘም ሰይፍ በእጁ ይዞ አየ፤ ሰገደም፥ በግምባሩም ወደ መሬት ተደፋ።


በለዓምም ምሳሌውን ይመስል ጀመር፥ እንዲህም አለ፦ “ባላቅ ሆይ! ተነሣ፥ ስማም፤ የሴፎር ልጅ ሆይ! አድምጠኝ፤


በለዓምም ምሳሌውን ይመስል ጀመር፥ እንዲህም አለ፦ “ባላቅ ከአራም አመጣኝ፥ የሞዓብ ንጉሥ ከምሥራቅ ተራሮች፤ ‘ና፥ ያዕቆብን ርገምልኝ፤ ና፥ እስራኤልን አውግዝልኝ አለኝ።’


እርሱም ምሳሌውን ይመስል ጀመር፥ እንዲህም አለ፦ “የቢዖር ልጅ በለዓም እንዲህ ይላል፥ ዐይኖቹ የተከፈቱለት ሰው እንዲህ ይላል፤


የጌታን ቃላት የሚሰማ፥ የልዑልንም እውቀት የሚያውቅ፥ ሁሉን የሚችል የአምላክን ራእይ የሚያይ፥ ወድቆ ሳለ ዐይኖቹ ግን የተከፈቱለት እንዲህ ይላል፦


የእግዚአብሔርን ቃላት የሚሰማ፥ ሁሉን የሚችል የአምላክን ራእይ የሚያይ፥ ወድቆም ሳለ ዐይኖቹ ግን የተከፈቱለት እንዲህ ይላል፦