La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




ዘኍል 24:2 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

በለዓምም ዓይኑን አንሥቶ እስራኤል በየነገዱ ተቀምጦ አየ፤ የእግዚአብሔርም መንፈስ በእርሱ ላይ መጣ።

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

በለዓም አሻግሮ ተመልክቶ እስራኤል በየነገድ በየነገዱ ሆኖ መስፈሩን ሲያይ የእግዚአብሔር መንፈስ በላዩ መጣበት፤

Ver Capítulo

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

የእስራኤል ሕዝብ በየነገዳቸው በቅደም ተከተል ተራ ሰፍረው አየ፤ የእግዚአብሔርም መንፈስ ስላደረበት፥

Ver Capítulo

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

በለ​ዓ​ምም ዐይ​ኑን አን​ሥቶ እስ​ራ​ኤል በየ​ነ​ገ​ዳ​ቸው ሲጓዙ አየ፤ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም መን​ፈስ በላዩ መጣ።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

በለዓምም ዓይኑን አንሥቶ እስራኤል በየነገዱ ተቀምጦ አየ፤ የእግዚአብሔርም መንፈስ በላዩ መጣ።

Ver Capítulo



ዘኍል 24:2
17 Referencias Cruzadas  

የጌታም መንፈስ በዖዴድ ልጅ በዓዛርያስ ላይ መጣ፤


ይህች እንደ ማለዳ ብርሃን የምትጐበኝ፥ እንደ ጨረቃ የተዋበች እንደ ፀሐይም የጠራች፥ ዓላማ ይዞ እንደ ተሰለፈ ሠራዊት የምታስፈራ ማን ናት?


ወዳጄ ሆይ፥ እንደ ቴርሳ ውብ ነሽ፥ እንደ ኢየሩሳሌምም ያማርሽ ነሽ፥ ዓላማ ይዞ እንደ ተሰለፈ ሠራዊት ታስፈሪያለሽ።


ያዕቆብ ሆይ! ድንኳኖችህ፥ እስራኤል ሆይ! ማደሪያዎችህ ምንኛ ያምራሉ!


ቀናኢው ስምዖንና አሳልፎ የሰጠው የአስቆሮቱ ይሁዳ።


በሽተኞችን ፈውሱ፤ ሙታንን አስነሡ፤ ለምጻሞችን አንጹ፤ አጋንንትን አስወጡ፤ በነጻ የተቀበላችሁትን በነጻ ስጡ።


በዚያ ቀን ብዙዎች ‘ጌታ ሆይ! ጌታ ሆይ! በስምህ ትንቢት አልተናገርንምን? በስምህስ አጋንንትን አላወጣንምን? በስምህስ ብዙ ተአምራትን አላደረግንምን?’ ይሉኛል።


ነገር ግን መናፍስት ስለ ተገዙላችሁ በዚህ ደስ አይበላችሁ፤ ይልቁንም ስማችሁ በሰማያት ሰለ ተጻፈ ደስ ይበላችሁ።”


በጌታ ቀን በመንፈስ ነበርሁ፤ በኋላዬም የመለከትን ድምፅ የሚመስል ታላቅ ድምፅ ሰማሁ፤


የጌታም መንፈስ በእርሱ ላይ ዐደረ፤ በእስራኤልም ላይ መሪ ሆነ፤ ለጦርነት በወጣ ጊዜ ጌታ የመስጴጦምያውን ንጉሥ ኩሽን ሪሽዓታይምን አሳልፎ ሰጠው፤ እርሱም ኩሽን-ሪሽዓታይምን ድል አደረገው።


ጊብዓ በደረሱ ጊዜ፥ እነሆ የነቢያቱ ጉባኤ አገኙት፤ የእግዚአብሔር መንፈስ በኃይል ወረደበት፤ ከእነርሱም ጋር ትንቢት ተናገረ።


ስለዚህ ዳዊትን እንዲይዙ ሰዎችን ላከ፤ እነርሱም የነቢያትም ጉባኤ በሳሙኤል መሪነት ትንቢት ሲናገሩ ባዩ ጊዜ፥ የእግዚአብሔር መንፈስ በሳኦል ሰዎች ላይ ወረደ፤ እነርሱም እንደዚሁ ትንቢት ተናገሩ።


ስለዚህ ሳኦል በራማ ወደምትገኘው ወደ የራማዋ ናዮት ሄደ፤ ሲሄድ ሳለም የእግዚአብሔር መንፈስ በእርሱም ላይ ደግሞ ወረደ፤ ወደ ናዮት እስኪደርስ ድረስም ትንቢት እየተናገረ ተጓዘ።