La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




ዘኍል 19:3 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

እርሷንም ለካህኑ ለአልዓዛር ትሰጣላችሁ፥ እርሷም ከሰፈር ወደ ውጭ ትወሰዳለች፥ እርሷም በእርሱ ፊት ትታረዳለች።

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

ለካህኑ ለአልዓዛርም ስጠው፤ ከሰፈሩ አውጥተውም በፊቱ ይረዷት።

Ver Capítulo

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

ጊደርዋንም ለካህኑ ለአልዓዛር ስጡት፤ ከሰፈርም ወጥታ በእርሱ ፊት ትታረድ፤

Ver Capítulo

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

እር​ስ​ዋ​ንም ለካ​ህኑ ለአ​ል​ዓ​ዛር ትሰ​ጠ​ዋ​ለህ፤ ከሰ​ፈር ወደ ውጭ ወደ ንጹሕ ስፍራ ይወ​ስ​ዷ​ታል፤ በፊ​ቱም ያር​ዷ​ታል።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

እርስዋንም ለካህኑ ለአልዓዛር ትሰጣላችሁ፥ እርስዋንም ከሰፈር ወደ ውጭ ይወስዳታል፥ አንድ ሰውም በፊቱ ያርዳታል።

Ver Capítulo



ዘኍል 19:3
11 Referencias Cruzadas  

ለማስተስረያም እንዲሆን ደማቸው ወደተቀደሰው ስፍራ የገባውን፥ የኃጢአቱን መሥዋዕት ወይፈንና የኃጢአቱን መሥዋዕት ፍየል ከሰፈሩ ውጭ ያወጡአቸዋል፤ ቆዳቸውንም፥ ሥጋቸውንም፥ ፈርሳቸውንም በእሳት ያቃጥላሉ።


“ተሳዳቢውን ከሰፈሩ ውጭ አውጣው፤ የሰሙትም ሁሉ እጃቸውን በራሱ ላይ ይጫኑበት፤ ማኅበሩም ሁሉ ይውገረው።


የወይፈኑን ቆዳ፥ ሥጋውንም ሁሉ፥ ራሱንም፥ እግሮቹንም፥ ሆድ ዕቃውንም፥ ፈርሱንም፥


ወይፈኑን ሁሉ ከሰፈሩ ውጭ አመድ ወደሚፈስበት ወደ ንጹሕ ስፍራ ይወስዳል፥ በእንጨትም ላይ በእሳት ያቃጥለዋል፤ አመድ በሚፈስስበት ስፍራ ይቃጠላል።


ወይፈኑንም ከሰፈሩ ውጭ ይወስዳል፥ የፊተኛውንም ወይፈን እንዳቃጠለ ያቃጥለዋል፤ ይህ የማኅበሩ የኃጢአት መሥዋዕት ነው።


ማኅበሩም ሁሉ ከሰፈሩ ወደ ውጭ አውጡት፥ ጌታም ሙሴን እንዳዘዘው በድንጋይ ወግረው ገደሉት።


ንጹሕም ሰው የጊደሪቱን አመድ ይሰበስባል ከሰፈሩም ውጭ በንጹሕ ስፍራ ያኖረዋል፤ ርኩሰትንም የሚያነጻ ውኃ ተደርጎ ለእስራኤል ልጆች ማኅበር ይጠበቃል፤ ከኃጢአት ለማንጻት የሚሆን ነው።


ናዳብና አብዩድ በሲና ምድረ በዳ በጌታ ፊት ያልተፈቀደውን እሳት ባቀረቡ ጊዜ በጌታ ፊት ሞቱ፤ ልጆችም አልነበሩአቸውም። አልዓዛርና ኢታምር በአባታቸው በአሮን ፊት በክህነት ያገለግሉ ነበር።


“የእስራኤል ልጆች የለምጽ ደዌ ያለበትን ሁሉ፥ ፈሳሽ ነገርም ያለበትን ሁሉ፥ ሬሳንም በመንካት የረከሰውን ሁሉ ከሰፈሩ እንዲያወጡ እዘዛቸው፤