La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




ዘኍል 17:7 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

ሙሴም በትሮቹን በጌታ ፊት በምስክሩ ድንኳን ውስጥ አኖራቸው።

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

ሙሴም በትሮቹን ወስዶ በምስክሩ ድንኳን ውስጥ በእግዚአብሔር ፊት አኖራቸው።

Ver Capítulo

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

ሙሴ በትሮቹን ሁሉ ወስዶ በድንኳኑ ውስጥ በእግዚአብሔር ቃል ኪዳን ታቦት ፊት ለፊት አኖራቸው።

Ver Capítulo

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

ሙሴም በት​ሮ​ቹን በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት በም​ስ​ክሩ ድን​ኳን ውስጥ አኖ​ራ​ቸው።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

ሙሴም በትሮቹን በእግዚአብሔር ፊት በምስክሩ ድንኳን ውስጥ አኖራቸው።

Ver Capítulo



ዘኍል 17:7
9 Referencias Cruzadas  

በሙሴ ትእዛዝ መሠረት የሌዋውያን አገልግሎት ሊሆን በካህኑ በአሮን ልጅ በኢታማር እጅ የተቆጠረው የማደሪያው፥ የምስክሩ ማደሪያ፥ ዕቃ ድምር ይህ ነው።


ነገር ግን በምስክሩ ማደሪያና በዕቃው ሁሉ የእርሱም በሆነው ነገር ሁሉ ላይ ሌዋውያንን ሹማቸው። ማደሪያውንና ዕቃዎቹን ሁሉ ይሸከሙ፥ ያገልግሉትም፥ በማደሪያውም ዙሪያ ይስፈሩ።


ነገር ግን በእስራኤል ልጆች ጉባኤ ላይ ቁጣ እንዳይወርድ ሌዋውያን በምስክሩ ማደሪያ ዙሪያ ይስፈሩ፤ ሌዋውያንም የምስክሩን ማደሪያ ይጠብቁ።”


ማኅበሩ ሁሉ ግን በድንጋይ ሊወግሯቸው ተማከሩ። የጌታም ክብር ለእስራኤል ልጆች ሁሉ በመገናኛው ድንኳን ተገለጠ።


እኔ ከእናንተ ጋር በምገናኝበት በመገናኛው ድንኳን ውስጥ በምስክሩ ፊት ለፊት አኑራቸው።


ሙሴም ለእስራኤል ልጆች ተናገረ፤ አለቆቻቸው ሁሉ ዐሥራ ሁለት በትሮች፥ እያንዳንዱም አለቃ በየአባቱ ቤት አንድ አንድ በትር፥ ሰጡት፤ የአሮንም በትር በበትሮቻቸው መካከል ነበረች።


እንዲሁም አንተ ከአንተም ጋር ልጆችህ በምስክሩ ድንኳን ፊት ሳላችሁ ከአንተ ጋር በአንድነት እንዲሆኑ፥ እንዲያገለግሉህም፥ የአባትህን የሌዊን ነገድ ወንድሞችህን ደግሞ ከአንተ ጋር አምጣቸው።


ማደሪያውም በተተከለ ቀን ደመናው ማደሪያውን፥ የምስክሩን ድንኳን ሸፈነው፤ ከማታም ጀምሮ እስከ ጥዋት ድረስ በማደሪያው ላይ ነበረ፤ እርሱም እንደ እሳት ያለ አምሳል ነበረ።


“እንዳየው ምስል አድርጎ ይሠራት ዘንድ ሙሴን ተናግሮ እንዳዘዘው፥ የምስክር ድንኳን ከአባቶቻችን ዘንድ በምድረ በዳ ነበረች፤