ነህምያ 7:67 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ከወንድ አገልጋዮቻቸውና ከሴት አገልጋዮቻቸው ሌላ፥ ሰባት ሺህ ሦስት መቶ ሠላሳ ሰባት ነበሩ፥ ሁለት መቶ አርባ አምስት ወንዶችና ሴቶች መዘምራንም ነበሩአቸው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ይህም 7,337 ከሚሆኑት ከወንዶችና ከሴቶች አገልጋዮቻቸው በተጨማሪ ነው፤ 245 ወንዶችና ሴቶች መዘምራን ነበሯቸው። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ይኸውም ሰባት ሺህ ሦስት መቶ ሠላሳ ሰባት ከነበሩ ከሎሌዎቻቸውና ከገረዶቻቸው ሌላ ሁለት መቶም አርባ አምስት ወንዶች መዘምራንና ሴቶች መዘምራት ነበሩአቸው። |
በተጨማሪም ወንዶች አገልጋይዮቻቸውና ሴቶች አገልጋዮቻቸው እነዚህ ሰባት ሺህ ሦስት መቶ ሠላሳ ሰባት ነበሩ ሌላ ሁለት መቶ ወንዶች መዘምራንና ሴቶች መዘምራን ነበሩአቸው።
በራሱ ምድር ላይ መውደቅያው እስከሚመጣ ጊዜ ድረስ አሕዛብ ሁሉ ለእርሱና ለልጁም ለልጅ ልጁም ያገለግላሉ፤ ከዚያም በኋላ ብዙ አሕዛብና ታላላቆች ነገሥታት እርሱን አገልጋይ ያደርጉታል።