ነህምያ 7:64 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እነዚህ በትውልድ መጽሐፍ ትውልዳቸውን ፈለጉ፥ ነገር ግን አልተገኘም፤ ከክህነትም ተከለከሉ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እነዚህ በትውልድ መዝገቡ ውስጥ የቤተ ሰባቸውን ዝርዝር ፈለጉ፤ ነገር ግን ሊያገኙት አልቻሉም፤ ስለዚህ እንዳልነጹ ተቈጥረው ከክህነት ተከለከሉ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እነዚህ በትውልድ መጽሐፍ ትውልዳቸውን ፈለጉ፤ ነገር ግን አልተገኘም፤ ከክህነትም ተከለከሉ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እነዚህ በትውልድ መጽሐፍ ትውልዳቸውን ፈለጉ፥ ነገር ግን አልተገኘም፥ ከክህነትም ተከለከሉ። |
አምላኬም መኳንንቱን፥ ሹማምቱንና ሕዝቡን ሰብስቤ እንድቆጥራቸው በልቤ አስቀመጠ፤ አስቀድመው የመጡትን ሰዎች የትውልድ መጽሐፋቸውን አገኘሁ፥ በእርሱም እንደዚህ ተጽፎ አገኘሁ።
ከካህናቱም የሐባያ ልጆች፥ የሃቆጽ ልጆች፥ የባርዚላይ ልጆች እሱም ከገለዓዳዊው የባርዚላይ ሴቶች ልጆች ሚስት ያገባ፥ በስማቸውም የተጠራ ነው።
የተቀባውም ካህን ኃጢአት ሠርቶ በሕዝቡ ላይ በደል ቢያመጣ፥ ስለ ሠራው ኃጢአቱ ነውር የሌለበት ወይፈን ለጌታ ለኃጢአት መሥዋዕት ያቀርባል።