ከዚያም በኋላ ወደ ሕዝቅያስ መልእክት ላኩበት፤ ሕዝቅያስም ባለሟሎቹ የሆኑ ሦስት ባለ ሥልጣኖች ሄደው እንዲገናኙአቸው አዘዘ፤ እነርሱም የቤተ መንግሥቱ ኃላፊ የሆነ የሒልቂያ ልጅ ኤልያቄም፥ እንዲሁም የቤተ መንግሥት ጸሐፊ የሆነው ሼብናና የቤተ መዛግብት ኃላፊ የሆነው የአሳፍ ልጅ ዮአሕ ነበሩ፤
ነህምያ 12:7 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ሳሉ፥ ዓሞቅ፥ ሒልቂያ፥ ይዳዕያ፤ እነዚህ በኢያሱ ዘመን የካህናቱና የወንድሞቻቸው መሪዎች ነበሩ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ሰሉ፣ ዓሞቅ፣ ኬልቅያስና ዮዳኤ። እነዚህ በኢያሱ ዘመን የካህናቱና የወንድሞቻቸው አለቆች ነበሩ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ሳሎም፥ ዓሞቅ፥ ሔልቅያስ፥ ኢዳዕያ፤ እነዚህ በኢያሱ ዘመን የካህናቱና የወንድሞቻቸው አለቆች ነበሩ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ሰሉ፥ ዓሞቅ፥ ኬልቅያስ፥ ዮዳኤ፥ እነዚህ በኢያሱ ዘመን የካህናቱና የወንድሞቻቸው አለቆች ነበሩ። |
ከዚያም በኋላ ወደ ሕዝቅያስ መልእክት ላኩበት፤ ሕዝቅያስም ባለሟሎቹ የሆኑ ሦስት ባለ ሥልጣኖች ሄደው እንዲገናኙአቸው አዘዘ፤ እነርሱም የቤተ መንግሥቱ ኃላፊ የሆነ የሒልቂያ ልጅ ኤልያቄም፥ እንዲሁም የቤተ መንግሥት ጸሐፊ የሆነው ሼብናና የቤተ መዛግብት ኃላፊ የሆነው የአሳፍ ልጅ ዮአሕ ነበሩ፤
የዮፃዳቅም ልጅ ኢያሱ ተነሣ፥ ወንድሞቹ ካህናትና፥ የሸአልቲኤል ልጅ ዘሩባቤልና ወንድሞቹም በእግዚአብሔር ሰው በሙሴ ሕግ እንደ ተጻፈ የሚቃጠለውን መሥዋዕት ሊያቀርቡበት የእስራኤልን አምላክ መሠዊያ ሠሩ።
በንጉሡ በዳርዮስ በሁለተኛው ዓመት በስድስተኛው ወር ከወሩም በመጀመሪያው ቀን የጌታ ቃል በነቢዩ በሐጌ እጅ ወደ ይሁዳ ገዢ ወደ ሰላትያል ልጅ ወደ ዘሩባቤልና ወደ ታላቁ ካህን ወደ ኢዮሴዴቅ ልጅ ወደ ኢያሱ እንዲህ ሲል መጣ፦