ናሆም 3:7 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የሚያይሽም ሁሉ ከአንቺ ሸሽቶ፦ ነነዌ ወድማለች፤ ማን ያዝንላታል? አንቺን የሚያጽናኑ ከወዴት እፈልጋለሁ? ይላል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም የሚያዩሽ ሁሉ ከአንቺ እየሸሹ፣ ‘ነነዌ ፈራርሳለች፤ ማን ያለቅስላታል?’ ይላሉ፤ የሚያጽናናሽንስ ከወዴት አገኛለሁ?” አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የሚያይሽ ሁሉ በመሸማቀቅ ‘እነሆ ነነዌ ፈራርሳ ውድማ ሆናለች፤ ማን ያዝንላታል?’ ይላል። የሚያጽናናትስ እኔ ከወዴት አገኝላታለሁ?” የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የሚያይሽም ሁሉ ከአንቺ ሸሽቶ፦ ነነዌ ባድማ ሆናለች፣ የሚያለቅስላትስ ማን ነው? የሚያጽናናትንስ ከወዴት እፈልጋለሁ? ይላል። |
ስለዚህ የእስራኤል አምላክ የሠራዊት ጌታ እንዲህ ይላል፦ የአሦርን ንጉሥ እንደ ቀጣሁ እንዲሁ፥ እነሆ፥ የባቢሎንን ንጉሥና ምድሩን እቀጣለሁ።
ባቢሎንን ልንፈውሳት ሞከርን፥ እርሷ ግን አልተፈወሰችም፤ ፍርድዋ እስከ ሰማይ ደርሶአልና፥ እስከ ደመናም ድረስ ከፍ ከፍ ብሏልና ትታችኋት እያንዳንዳችን ወደ አገራችን እንሂድ።
ሜም። የኢየሩሳሌም ሴት ልጅ ሆይ፥ ምን እመሰክርልሻለሁ? በምንስ እመስልሻለሁ? ድንግሊቱ የጽዮን ልጅ ሆይ፥ አጽናናሽ ዘንድ በምን አስተካክልሻለሁ? ስብራትሽ እንደ ባሕር ታላቅ ነውና፥ የሚፈውስሽ ማን ነው?
ሥቃይዋንም ከመፍራት የተነሣ በሩቅ ቆመው “አንቺ ታላቂቱ ከተማ! ብርቱይቱ ከተማ ባቢሎን! ወዮልሽ! ወዮልሽ! በአንድ ሰዓት ውስጥ ፍርድሽ ይፈጸማልና፤” እያሉ ይናገራሉ።