Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




ሰቈቃወ 2:13 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

13 ሜም። የኢየሩሳሌም ሴት ልጅ ሆይ፥ ምን እመሰክርልሻለሁ? በምንስ እመስልሻለሁ? ድንግሊቱ የጽዮን ልጅ ሆይ፥ አጽናናሽ ዘንድ በምን አስተካክልሻለሁ? ስብራትሽ እንደ ባሕር ታላቅ ነውና፥ የሚፈውስሽ ማን ነው?

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

13 የኢየሩሳሌም ሴት ልጅ ሆይ፤ ስላንቺ ምን ማለት እችላለሁ? ከምንስ ጋራ አወዳድርሻለሁ? ድንግሊቱ የጽዮን ልጅ ሆይ፤ አጽናናሽ ዘንድ፣ በምን ልመስልሽ እችላለሁ? ቍስልሽ እንደ ባሕር ጥልቅ ነው፤ ማንስ ሊፈውስሽ ይችላል?

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

13 ምን ልበላችሁ? ከምንስ ጋር ላነጻጽራችሁ? የተወደደችው ከተማ የኢየሩሳሌም ሕዝብ ሆይ! እንዳጽናናችሁ ከምን ጋር ላመሳስላችሁ? በተለይ የኢየሩሳሌም ከተማ ሕዝብ ሆይ! የሚደርስባችሁ ጥፋት እንደ ባሕር መጠኑ ሰፊ ስለ ሆነ፥ ማን ሊፈውሳችሁ ይችላል?

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

13 ሜም። የኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም ሴት ልጅ ሆይ፥ ምን እመ​ሰ​ክ​ር​ል​ሻ​ለሁ? በም​ንስ እመ​ስ​ል​ሻ​ለሁ? ድን​ግ​ሊቱ የጽ​ዮን ልጅ ሆይ፥ ማን ያድ​ን​ሻል? ማንስ ያጽ​ና​ና​ሻል? ስብ​ራ​ትሽ እንደ ባሕር ታላቅ ነውና፤ የሚ​ፈ​ው​ስሽ ማን ነው?

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

13 ሜም። የኢየሩሳሌም ሴት ልጅ ሆይ፥ ምን እመሰክርልሻለሁ? በምንስ እመስልሻለሁ? ድንግሊቱ የጽዮን ልጅ ሆይ፥ አጽናናሽ ዘንድ በምን አስተካክልሻለሁ? ስብራትሽ እንደ ባሕር ታላቅ ነውና፥ የሚፈውስሽ ማን ነው?

Ver Capítulo Copiar




ሰቈቃወ 2:13
14 Referencias Cruzadas  

ላሜድ። እናንተ መንገድ አላፊዎች ሁሉ፥ በእናንተ ዘንድ ምንም የለምን? እግዚአብሔር በጽኑ ቁጣው ቀን እኔን እንዳስጨነቀበት በእኔ ላይ እንደተደረገው እንደ እኔ መከራ የሚመስል መከራ እንዳለ ተመልከቱ፥ እዩ።


ይህን ቃል እንዲህ ብለህ ንገራቸው፦ ‘የወገኔ ልጅ ድንግሊቱ በታላቅ ስብራትና ፈጽሞ በማይሽር ቁስል ቆስላለችና ዐይኖቼ ሌሊትና ቀን ሳያቋርጡ እንባ ያፍስሱ።


በገለዓድ የሚቀባ መድኃኒት የለምን? ወይስ በዚያ ሐኪም የለምን? የወገኔ ሴት ልጅ ፈውስ ስለምን አልሆነም?


ስለዚህም ዳዊት ወደ ባዓል ፈራጺም ሄዶ ፍልስጥኤማውያንን ድል አደረጋቸው። እርሱም “የጐርፍ ውሃ ጥሶ በመውጣት እንደሚያፈራርስ፥ ጌታም ጠላቶቼን በፊቴ አፈራረሳቸው” አለ። በዚህ የተነሣም የዚያ ቦታ ስም ባዓል ፈራጺም ተባለ።


ጌታ ስለ እርሱ የተናገረው ቃል ይህ ነው፦ ‘ድንግሊቱ የጽዮን ልጅ ቀላል አድርጋሃለች፥ በንቀትም ስቃብሃለች፤ የኢየሩሳሌም ልጅ ስትሸሽ ራስዋን ነቅንቃብሃለች።


የሶርያን ሁለቱን ወንዞችና የሶርያን ሶባልን ባቃጠለ ጊዜ ኢዮአብም ተመልሶ ከኤዶማውያን ሰዎች በጨው ሸለቆ ዐሥራ ሁለት ሺህ በገደለ ጊዜ፥


ስለ እርሱ እግዚአብሔር የተናገረው ቃል ይህ ነው፦ የጽዮን ድንግል ትንቅሃለች፤ ታፌዝብሃለች፤ አንተ እየሸሸህ ሳለህ፥ የኢየሩሳሌም ልጃገረዶች ከኋላህ ሆነው ራሳቸውን ይነቀንቁብሃል።


ዐይኖቻችንም እንባ እንዲያፈስሱ የዓይናችንም ሽፋሽፍቶች ውኃን እንዲያፈልቁ ፈጥነው ለእኛ ልቅሶውን ያነሳሱ።


በውኑ ይሁዳን ፈጽመህ ጥለኸዋልን? ነፍስህስ ጽዮንን ጠልታታለችን? ስለምን መታኸን? ፈውስስ ስለምን የለንም? ሰላምን በተስፋ ተጠባበቅን፥ መልካምም አልተገኘም፤ ፈውስን በተስፋ ተጠባበቅን፥ እነሆም፥ ድንጋጤ ሆነ።


በሰይፍ የተገደሉ ፈርዖንና ሠራዊቱ ሁሉ ያዩአቸዋል ፈርዖንም ስለ ብዛቱ ሁሉ ይጽናናል፥ ይላል ጌታ እግዚአብሔር።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios