Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




ናሆም 3:7 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም

7 የሚያዩሽ ሁሉ ከአንቺ እየሸሹ፣ ‘ነነዌ ፈራርሳለች፤ ማን ያለቅስላታል?’ ይላሉ፤ የሚያጽናናሽንስ ከወዴት አገኛለሁ?”

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

7 የሚያይሽም ሁሉ ከአንቺ ሸሽቶ፦ ነነዌ ወድማለች፤ ማን ያዝንላታል? አንቺን የሚያጽናኑ ከወዴት እፈልጋለሁ? ይላል።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

7 የሚያይሽ ሁሉ በመሸማቀቅ ‘እነሆ ነነዌ ፈራርሳ ውድማ ሆናለች፤ ማን ያዝንላታል?’ ይላል። የሚያጽናናትስ እኔ ከወዴት አገኝላታለሁ?”

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

7 የሚያይሽም ሁሉ ከአንቺ ሸሽቶ፦ ነነዌ ባድማ ሆናለች፣ የሚያለቅስላትስ ማን ነው? የሚያጽናናትንስ ከወዴት እፈልጋለሁ? ይላል።

Ver Capítulo Copiar




ናሆም 3:7
12 Referencias Cruzadas  

እነሆ፤ በጥፋት ላይ ጥፋት መጥተውብሻል፤ ታዲያ ማን ያጽናናሻል? እነርሱም መፈራረስና ጥፋት፣ ራብና ሰይፍ ናቸው፤ ታዲያ ማን ያስተዛዝንሽ?


“ኢየሩሳሌም ሆይ፤ የሚራራልሽ ማን ነው? ማንስ ያለቅስልሻል? ደኅንነትሽንስ ማን ጐራ ብሎ ይጠይቃል?


ስለዚህ የእስራኤል አምላክ የሰራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ “የአሦርን ንጉሥ እንደ ቀጣሁት ሁሉ፣ የባቢሎንን ንጉሥና ምድሩን እቀጣለሁ።


“ ‘ባቢሎንን ለመፈወስ ሞክረን ነበር፤ እርሷ ግን ልትፈወስ አትችልም፤ ፍርዷ እስከ ሰማይ ስለ ደረሰ፣ እስከ ደመናም ድረስ ከፍ ስላለ፣ ትተናት ወደየአገራችን እንሂድ።’


የኢየሩሳሌም ሴት ልጅ ሆይ፤ ስላንቺ ምን ማለት እችላለሁ? ከምንስ ጋራ አወዳድርሻለሁ? ድንግሊቱ የጽዮን ልጅ ሆይ፤ አጽናናሽ ዘንድ፣ በምን ልመስልሽ እችላለሁ? ቍስልሽ እንደ ባሕር ጥልቅ ነው፤ ማንስ ሊፈውስሽ ይችላል?


ስለ ነነዌ ጥፋት የተነገረ ንግር፤ የኤልቆሻዊው የናሆም የራእዩ መጽሐፍ ይህ ነው፤


እጁን በሰሜን ላይ ይዘረጋል፤ አሦርንም ያጠፋል፤ ነነዌን ፍጹም ባድማ፣ እንደ ምድረ በዳም ደረቅ ያደርጋታል።


ከጩኸታቸውም የተነሣ በአካባቢያቸው የነበሩት እስራኤላውያን ሁሉ፣ “ምድሪቱ እኛንም እኮ ልትውጠን ነው” ብለው ሸሹ።


ሥቃይዋንም በመፍራት በሩቅ ቆመው እንዲህ ይላሉ፤ “ ‘አንቺ ታላቂቱ ከተማ ወዮልሽ! ወዮልሽ! አንቺ ባቢሎን ብርቱዪቱ ከተማ፣ ፍርድሽ በአንድ ሰዓት ውስጥ መጥቷል።’


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos