La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




ናሆም 2:5 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

ሰረገሎች በመንገድ ላይ ይከንፋሉ፥ በአደባባዮችም ወዲህና ወዲያ ይጣደፋሉ፤ መልካቸው እንደ ፋና ነው፥ እንደ መብረቅም ይወረወራሉ።

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

ምርጥ ተዋጊዎቹን ይጠራል፤ ዳሩ ግን መንገድ ላይ ይሰናከላሉ፤ ወደ ከተማዪቱ ቅጥር ይሮጣሉ፤ መከላከያ ጋሻውም በቦታው አለ።

Ver Capítulo

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

እርሱ የጦር ሹማምንቱን ይጠራል፤ እነርሱም እየተደናቀፉ ወደፊት ይመጣሉ፤ የጠላት ወታደሮች እየሮጡ ወደ ከተማይቱ ቅጽር ይወጣሉ፤ የሚወረወርባቸውንም ፍላጻ በትልቁ ጋሻቸው ይከላከላሉ።

Ver Capítulo

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

መሳፍንቱን ያስባል፣ በአረማመዳቸው ይሰናከላሉ፣ ፈጥነው በቅጥርዋ ላይ ይወጣሉ፥ መጠጊያም ተዘጋጀለት።

Ver Capítulo



ናሆም 2:5
9 Referencias Cruzadas  

ማዕዱን ያዘጋጃሉ፥ ምንጣፉንም ይዘረጋሉ፥ ይበላሉም፥ ይጠጣሉም፤ እናንተ መሳፍንት ሆይ፥ ተነሡ፥ ጋሻውን አዘጋጁ።


በመካከላቸው ደካማና ስንኩል አይገኝም፤ የሚያንቀላፋና የሚተኛ አይኖርም፤ የወገባቸው መቀነት አይላላም፤ የጫማቸውም ማሰሪያ አይበጠስም።


ኃያሉ በኃያሉ ላይ ተሰናክሎ ሁለቱ በአንድነት ወድቀዋልና አሕዛብ ውርደትሽን ሰምተዋል፥ ልቅሶሽም ምድርን ሞልቶአታል።


ቀስትን የሚገትሩትን ቀስተኞችን ሁሉ በባቢሎን ላይ ጥሩአቸው፤ በዙሪያዋ ስፈሩባት አንድም ሰው አያምልጥ፤ በእስራኤል ቅዱስ በጌታ ላይ በኩራት አልታዘዝም ብላለችና እንደ ሥራዋ መጠን መልሱላት፥ እንዳደረገችም ሁሉ አድርጉባት።


መሳፍንቱን ያስባል፤ በአረማመዳቸው ይሰናከላሉ፤ ፈጥነው ወደ ቅጥርዋ ይሮጣሉ፥ መጠለያም ተዘጋጅቷል።


የአሦር ንጉሥ ሆይ፥ እረኞችህ አንቀላፍተዋል፤ መኳንንቶችህም ዐርፈዋል፤ ሕዝብህ በተራሮች ላይ ተበትነዋል፥ የሚሰበስባቸውም የለም።


ፈረሰኛው ይጋልባል፥ ሰይፍ ይንቦገቦጋል፥ ጦር ይብለጨለጫል የተገደለ ብዛት፥ የበድን ክምር፥ ሬሳው ማለቂያ የለውም፤ በሬሳቸውም ይሰናከላሉ።


ፈረሶቻቸው ከነብር ይልቅ ፈጣኖች ናቸው፥ ከማታም ተኩላ ይልቅ አስፈሪዎች ናቸው፤ ፈረሰኞቻቸውም ይንሳፈፋሉ፥ ፈረሰኞቻቸው ከሩቅ ይመጣሉ፥ ለመንጠቅ እንደሚቸኩል ንስር ይበርራሉ።