ሚክያስ 6:11 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የክፋት ሚዛንንና የአታላይ መመዘኛ ከረጢት አነጻለሁን? አዲሱ መደበኛ ትርጒም አባይ ሚዛን የያዘውን ሰው፣ ሐሰተኛ መመዘኛ በከረጢት የቋጠረውን ንጹሕ ላድርገውን? አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ታዲያ በሐሰተኛ ሚዛንና መስፈሪያ የሚጠቀሙትን ሰዎች እታገሣለሁን? የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በአባይ ሚዛንና በከረጢት ባለ በተንኰል መመዘኛ ንጹሕ እሆናለሁን? መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በአባይ ሚዛንና በከረጢት ባለ በተንኰል መመዘኛ ንጹሕ እሆናለሁን? |
ትክክለኛም ሚዛን፥ ትክክለኛም መመዘኛ፥ ትክክለኛም የኢፍ መስፈሪያ፥ ትክክለኛም የኢን መስፈሪያ ይኑሩአችሁ፤ ከግብጽ ምድር ያወጣኋችሁ እኔ ጌታ አምላካችሁ ነኝ።
እናንተ እንዲህ ትላላችሁ፦ “እህልን እንድንሸጥ መባቻው መቼ ያልፋል? ስንዴውንም ለሽያጭ ገበያ ለማቅረብ ሰንበት መቼ ያበቃል? የኢፍ መስፈሪያውንም እናሳንሳለን፥ ሰቅሉንም እናበዛለን፥ በሐሰተኛም ሚዛን እናታልላለን፥