ሚክያስ 6:10 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በክፉ ቤት የክፋት መዝገብ፥ አስጸያፊ ሐሰተኛ መስፈሪያ አሁንም አለን? አዲሱ መደበኛ ትርጒም የክፋት ቤት ሆይ፤ በግፍ የተገኘ ሀብታችሁን፣ በሐሰተኛ መስፈሪያ የሰበሰባችሁትን አስጸያፊ ነገር እረሳዋለሁን? አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ኃጢአተኛ በቤቱ በክፋት የሰበሰበውን ሀብትና የተረገመውን ሐሰተኛ ሚዛን ልረሳቸው እችላለሁን? የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በውኑ በኃጢአተኛ ቤት የኃጢአት መዝገብ፥ የተጸየፈውም ውሸተኛ መስፈሪያ ገና አለ ይሆን? መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በውኑ በኃጢአተኛ ቤት የኃጢአት መዝገብ፥ የተጸየፈውም ውሸተኛ መስፈሪያ ገና አለ ይሆን? |
በአዛጦን የንጉሥ ቅጥሮችና በግብጽ ምድር ባሉ የንጉሥ ቅጥሮች ላይ አውጁ እንዲህም በሉ፦ “በሰማርያ ተራሮች ላይ ተሰብሰቡ፥ በመካከልዋም የሆነውን ታላቁን ውካታ፥ በውስጧም ያለውን ግፍ ተመልከቱ።”
እኔም፦ “ምንድን ናት?” አልኩት። እርሱም፦ “ይህች የምትወጣው የኢፍ መስፈሪያ ናት” አለኝ። ደግሞም፦ “ይህ ነው በምድር ሁሉ ያለ የእነርሱ በደል” አለ።
የእስራኤል ልጆች ግን እርም በሆነው ነገር በደሉ፤ ከይሁዳ ነገድ የሆነ አካን፥ እርሱም የከርሚ ልጅ፥ የዘንበሪ ልጅ፥ የዛራ ልጅ፥ እርም ከሆነው ነገር ወሰደ፤ የጌታም ቁጣ በእስራኤል ልጆች ላይ ነደደ።