ሚክያስ 1:15 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በማሬሻ የምትቀመጪ ሆይ፥ ወራሽ አመጣብሻለሁ፤ የእስራኤል ክብር ወደ ዓዱላም ይመጣል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እናንተ በመሪሳ የምትኖሩ ድል አድራጊ አመጣባችኋለሁ፤ ያ የእስራኤል ክብር የሆነው ወደ ዓዶላም ይመጣል። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የመሪሳ ሕዝብ ሆይ! ወራሪ ጠላት አመጣባችኋለሁ፤ የተከበሩ የእስራኤል መሪዎችም በዐዱላም ዋሻ ይሸሸጋሉ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በመሪሳ የምትቀመጪ ሆይ፥ ወራሽ አመጣብሻለሁ፥ የእስራኤል ክብር ወደ ዓዶላም ይመጣል። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በመሪሳ የምትቀመጪ ሆይ፥ ወራሽ አመጣብሻለሁ፥ የእስራኤል ክብር ወደ ዓዶላም ይመጣል። |
በምትጎበኙበት ቀን ምን ይውጣችኋል? ጥፋት ከሩቅ ሲመጣስ ምን ትሆናላችሁ? ርዳታን ለማግኘትስ ወደ ማን ትሸሻላችሁ? ሀብታችሁንስ የት ታገኙታላችሁ?
ስለ አሞን ልጆች፤ ጌታ እንዲህ ይላል፦ ለእስራኤል ልጆች የሉትምን? ወይስ ወራሽ የለውምን? ታዲያ ሚልኮምስ ጋድን ለምን ወረሰ? ሕዝቡስ በከተሞቹ ላይ ለምን ተቀመጠ?