ሚክያስ 1:10 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በጋት አታውሩት፥ በፍጹም አታልቅሱ፤ በቤትልዓፍራ በትቢያ ላይ ተንከባለሉ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም በጋት አታውሩት፤ ከቶም አታልቅሱ፤ በቤትዓፍራ፣ በትቢያ ላይ ተንከባለሉ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በጌት ላሉት ጠላቶቻችን የደረሰብንን መከራ አትንገሩአቸው፤ በዚያም ፈጽሞ አታልቅሱ፤ በቤትዖፍራ በሚገኙት ወገኖቻችን መካከል ግን በትቢያ ላይ እየተንከባለላችሁ አልቅሱ! የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በጌት ላይ አታውሩ፥ በአኮ ላይ እንባን አታድርጉ፥ በቤትዓፍራ በትቢያ ላይ ተንከባለሉ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በጌት ላይ አታውሩ፥ በአኮ ላይ እንባን አታድርጉ፥ በቤትዓፍራ በትቢያ ላይ ተንከባለሉ። |
የሕዝቤ ሴት ልጅ ሆይ! ማቅ ልበሺ፥ በአመድም ውስጥ ተንከባለዪ፤ አጥፊ በላያችን በድንገት ይመጣብናልና ለአንድያ ልጅ እንደሚደረግ ልቅሶ፥ መራራ ልቅሶ አልቅሺ።
የሞተውን ሰው የሚያቃጥለው ዘመዱ አጥንቱን ከቤቱ አንስቶት ባወጣው ጊዜ፥ በቤቱም በውስጠኛው ክፍል ያለውን፦ “በእዚያ እስከ አሁን ድረስ ከአንተ ጋር ሰው አለን?” ይለዋል፥ እርሱም፦ “ማንም የለም” ይላል፤ ያንጊዜ፦ “የጌታን ስም ልንጠራ አይገባንምና ዝም በል” ይለዋል።