Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




ሚክያስ 1:10 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም

10 በጋት አታውሩት፤ ከቶም አታልቅሱ፤ በቤትዓፍራ፣ በትቢያ ላይ ተንከባለሉ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

10 በጋት አታውሩት፥ በፍጹም አታልቅሱ፤ በቤትልዓፍራ በትቢያ ላይ ተንከባለሉ።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

10 በጌት ላሉት ጠላቶቻችን የደረሰብንን መከራ አትንገሩአቸው፤ በዚያም ፈጽሞ አታልቅሱ፤ በቤትዖፍራ በሚገኙት ወገኖቻችን መካከል ግን በትቢያ ላይ እየተንከባለላችሁ አልቅሱ!

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

10 በጌት ላይ አታውሩ፥ በአኮ ላይ እንባን አታድርጉ፥ በቤትዓፍራ በትቢያ ላይ ተንከባለሉ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

10 በጌት ላይ አታውሩ፥ በአኮ ላይ እንባን አታድርጉ፥ በቤትዓፍራ በትቢያ ላይ ተንከባለሉ።

Ver Capítulo Copiar




ሚክያስ 1:10
7 Referencias Cruzadas  

“ይህን በጋት አትናገሩ፤ በአስቀሎናም መንገዶች አታውጁት፤ የፍልስጥኤም ቈነጃጅት አይደሰቱ፤ ያልተገረዙት ሴቶች ልጆች እልል አይበሉ።


ኢዮብም ገላውን ለማከክ ገል ወሰደ፤ በዐመድም ላይ ተቀመጠ።


የሕዝቤ ልጅ ሆይ፤ ማቅ ልበሺ፤ በዐመድም ላይ ተንከባለዪ፤ አንድያ ልጁን እንዳጣ ሰው፣ ምርር ብለሽ አልቅሺ፤ አጥፊው በድንገት፣ በላያችን ይመጣልና።


ፊቱን በዐቧራ ውስጥ ይቅበር፤ ተስፋ ሊኖር ይችላልና።


ስለዚህ አስተዋይ ሰው በእንዲህ ያለ ጊዜ ዝም ይላል፤ ቀኖቹ ክፉዎች ናቸውና።


በድኖቹንም ከቤት አውጥቶ ማቃጠል ያለበት አንድ ዘመድ መጥቶ ተደብቆ ያለውን ሰው፣ “ከአንተ ጋራ የቀረ ሌላ ሰው አለን?” ሲለው፣ እርሱም “የለም” ይለዋል፤ ከዚያም በኋላ፣ “ዝም በል፤ የእግዚአብሔርን ስም መጥራት አይገባንም” ይለዋል።


ዓዊም፣ ዖፍራ፣ ኤፍራታ፣


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos