ሳዶቅም በዚያ ነበር፤ አብረውት የነበሩትም ሌዋውያን ሁሉ የእግዚአብሔርን ቃል ኪዳን ታቦት ተሸክመው መጡ፥ የእግዚአብሔርንም ታቦት፥ ሕዝቡ በሙሉ ከከተማዪቱ ለቆ እስኪ ወጣ ድረስ፥ አብያታር አጠገብ አስቀመጡ።
ማርቆስ 2:26 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) አብያታር ሊቀ ካህናት በነበረ ጊዜ ወደ እግዚአብሔር ቤት እንደ ገባ፥ ከካህናት በቀር መብላት ያልተፈቀደውን የመሥዋዕትን እንጀራ እንደ በላ፥ ከእርሱም ጋር ለነበሩት እንደሰጣቸው ከቶ አላነበባችሁምን?” አላቸው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም በሊቀ ካህናቱ በአብያታር ዘመን ወደ እግዚአብሔር ቤት ገብቶ፣ ካህናት ብቻ እንዲበሉት የተፈቀደውን ኅብስተ ገጽ ለርሱም ሆነ ዐብረውት ለነበሩትም ሰጣቸው።” አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም አብያታር የካህናት አለቃ በነበረበት ዘመን እርሱ ወደ እግዚአብሔር ቤት ገብቶ፥ ከካህናት በቀር ለሌሎች መብላት ያልተፈቀደውን፥ የተቀደሰውን የመባ ኅብስት በላ፤ ከእርሱም ጋር ለነበሩት ሰዎች ሰጣቸው።” የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) አብያተር ሊቀ ካህናት በነበረ ጊዜ ወደ እግዚአብሔር ቤት እንደ ገባ፥ ከካህናት በቀር መብላት ያልተፈቀደውን የመሥዋዕትን እንጀራ እንደ በላ፥ ከእርሱም ጋር ለነበሩት እንደ ሰጣቸው ከቶ አላነበባችሁምን?” አላቸው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ከካህናት በቀር መብላት ያልተፈቀደውን የመሥዋዕትን እንጀራ እንደ በላ፥ ከእርሱም ጋር ለነበሩት እንደ ሰጣቸው ከቶ አላነበባችሁምን? አላቸው። |
ሳዶቅም በዚያ ነበር፤ አብረውት የነበሩትም ሌዋውያን ሁሉ የእግዚአብሔርን ቃል ኪዳን ታቦት ተሸክመው መጡ፥ የእግዚአብሔርንም ታቦት፥ ሕዝቡ በሙሉ ከከተማዪቱ ለቆ እስኪ ወጣ ድረስ፥ አብያታር አጠገብ አስቀመጡ።
ንጉሡም “አቢሻግን በሚስትነት እንድድርለት ብቻ ለምን ትጠይቂኛለሽ? መንግሥቴንም ጭምር እንድለቅለት ለምን አልጠየቅሽኝም? እርሱ እኮ ታላቅ ወንድሜ ነው፤ ለምን ለካህኑ አብያታርና ለኢዮአብም ልዩ አስተያየት እንዳደርግላቸው አትጠይቂላቸውም!” አላት።
ከሌዊያውያንም ወገን የነበረው የናትናኤል ልጅ ጸሐፊው ሸማያ በንጉሡና በሹማምንቱ ፊት፥ በካህኑ በሳዶቅና በአብያታርም ልጅ በአቤሜሌክ ፊት፥ በካህናቱና በሌዋውያኑ አባቶች ቤቶች አለቆች ፊት ጻፋቸው፤ አንዱንም የአባት ቤት ለአልዓዛር፥ አንዱንም ለኢታምር ተመረጠ።
ዳዊትም ካህኑ አቢሜሌክ ወዳለበት ወደ ኖብ ሄደ። አቢሜሌክም እየተንቀጠቀጠ ዳዊትን ሊገናኘው መጣና፥ “ምነው ብቻህን? ሰውስ ለምን አብሮህ የለም?” ሲል ጠየቀው።