ማርቆስ 15:43 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የተከበረ የሸንጎ አባልና የእግዚአብሔርን መንግሥት ይጠባበቅ የነበረው የአርማትያሱ ዮሴፍ በድፍረት ወደ ጲላጦስ ሄዶ የኢየሱስን ሥጋ ለመነው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም የተከበረ የሸንጎ አባልና የእግዚአብሔርን መንግሥት ይጠባበቅ የነበረው የአርማትያሱ ዮሴፍ በድፍረት ወደ ጲላጦስ ሄዶ የኢየሱስን ሥጋ ለመነው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በዚያኑ ጊዜ የአይሁድ ሸንጎ አባል የነበረ ዮሴፍ የሚባል፥ የተከበረ የአርማትያስ ሰው መጣ። እርሱም የእግዚአብሔርን መንግሥት በተስፋ የሚጠባበቅ ሰው ነበር። በድፍረት ወደ ጲላጦስ ፊት ቀረበና የኢየሱስ አስከሬን እንዲሰጠው ለመነ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የከበረ አማካሪ የሆነ የአርማትያስ ዮሴፍ መጣ፤ እርሱም ደግሞ የእግዚአብሔርን መንግሥት ይጠባበቅ ነበር፤ ደፍሮም ወደ ጲላጦስ ገባና የኢየሱስን ሥጋ ለመነው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እርሱም ደግሞ የእግዚአብሔርን መንግሥት ይጠባበቅ ነበር፤ ደፍሮም ወደ ጲላጦስ ገባና የኢየሱስን ሥጋ ለመነው። |
እነሆም፥ በኢየሩሳሌም ስምዖን የሚባል አንድ ሰው ነበረ፤ ይህም ሰው የእስራኤልን መጽናናት የሚጠብቅ፥ ጻድቅና ትጉህም ነበረ፤ መንፈስ ቅዱስም በእርሱ ላይ ነበረ።
ይህም በምክራቸውና በሥራቸው አልተባበረም ነበር፤ አርማትያስም ከምትባል ከአይሁድ ከተማ ሆኖ እርሱ በበኩሉ የእግዚአብሔርን መንግሥት ይጠባበቅ ነበር።
ከዚህም በኋላ፥ አይሁድን በመፍራት በስውር የኢየሱስ ደቀመዝሙር የነበረው የአርማትያስ ዮሴፍ የኢየሱስን ሥጋ ለመውሰድ ጲላጦስን ለመነ፤ ጲላጦስም ፈቀደለት። ስለዚህም መጥቶ የኢየሱስን ሥጋ ወሰደ።
አይሁድ ግን የሚያመልኩትን የከበሩትንም ሴቶችና የከተማውን መኳንንት አወኩ፤ በጳውሎስና በበርናባስም ላይ ስደትን አስነሥተው ከአገራቸው አወጡአቸው።