Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




ማርቆስ 15:43 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

43 በዚያኑ ጊዜ የአይሁድ ሸንጎ አባል የነበረ ዮሴፍ የሚባል፥ የተከበረ የአርማትያስ ሰው መጣ። እርሱም የእግዚአብሔርን መንግሥት በተስፋ የሚጠባበቅ ሰው ነበር። በድፍረት ወደ ጲላጦስ ፊት ቀረበና የኢየሱስ አስከሬን እንዲሰጠው ለመነ።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

43 የተከበረ የሸንጎ አባልና የእግዚአብሔርን መንግሥት ይጠባበቅ የነበረው የአርማትያሱ ዮሴፍ በድፍረት ወደ ጲላጦስ ሄዶ የኢየሱስን ሥጋ ለመነው።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

43 የተከበረ የሸንጎ አባልና የእግዚአብሔርን መንግሥት ይጠባበቅ የነበረው የአርማትያሱ ዮሴፍ በድፍረት ወደ ጲላጦስ ሄዶ የኢየሱስን ሥጋ ለመነው።

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

43 የከበረ አማካሪ የሆነ የአርማትያስ ዮሴፍ መጣ፤ እርሱም ደግሞ የእግዚአብሔርን መንግሥት ይጠባበቅ ነበር፤ ደፍሮም ወደ ጲላጦስ ገባና የኢየሱስን ሥጋ ለመነው።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

43 እርሱም ደግሞ የእግዚአብሔርን መንግሥት ይጠባበቅ ነበር፤ ደፍሮም ወደ ጲላጦስ ገባና የኢየሱስን ሥጋ ለመነው።

Ver Capítulo Copiar




ማርቆስ 15:43
16 Referencias Cruzadas  

በዚያኑ ጊዜ እርስዋም መጥታ ጌታን ታመሰግን ጀመር፤ ስለ ሕፃኑም የኢየሩሳሌምን መዳን በተስፋ ለሚጠባበቁ ሁሉ ትናገር ነበር።


በዚያን ጊዜ በኢየሩሳሌም ስምዖን የሚባል አንድ ሰው ነበር፤ እርሱም ሕይወቱን ለእግዚአብሔር የሰጠ ጻድቅ ሰው ነበር፤ የእስራኤልን የመዳን ተስፋ ይጠባበቅ ነበር፤ መንፈስ ቅዱስም በእርሱ ላይ ነበር።


ይሁን እንጂ በአይሁድ ምክርና ሤራ አልተባበረም፤ እርሱ የእግዚአብሔርን መንግሥት በተስፋ የሚጠባበቅ ሰው ነበረ።


ስለዚህ ከእነርሱ ብዙዎች አመኑ፤ ብዙዎች የግሪክ ሀብታሞች ሴቶችና ብዙዎች ግሪካውያን ወንዶችም አመኑ።


የአይሁድ ባለሥልጣኖችን በመፍራት በስውር የኢየሱስ ደቀ መዝሙር የነበረው የአርማትያሱ ዮሴፍ የኢየሱስን አስከሬን ለመውሰድ ጲላጦስን ለመነ። ጲላጦስም ፈቀደለት። ስለዚህ ዮሴፍ ሄዶ አስከሬኑን ወሰደ።


በመሸ ጊዜ ዮሴፍ የሚባል አንድ የአርማትያስ ከተማ ሀብታም ሰው ወደዚያ መጣ፤ እርሱም የኢየሱስ ደቀ መዝሙር ነበረ፤


በእኔ መታሰር ምክንያት ከአማኞች ወንድሞች ብዙዎቹ በይበልጥ በጌታ የሚተማመኑ ሆነዋል፤ ስለዚህ የእግዚአብሔርን ቃል ያለ ፍርሀት ለማብሠር ከቀድሞ የበለጠ ድፍረት አግኝተዋል።


የአይሁድ መሪዎች ግን የአይሁድ እምነት ተከታዮች የሆኑትን ሀብታሞች ሴቶችና የከተማውን ታላላቅ ሰዎች አሳድመው በጳውሎስና በበርናባስ ላይ ስደት እንዲነሣ አደረጉ፤ ከአገራቸውም አስወጡአቸው።


ጴጥሮስም እስከ የካህናት አለቃው ግቢ ድረስ ኢየሱስን በሩቅ ይከተለው ነበር። እዚያም ከሎሌዎች ጋር ተቀምጦ እሳት ይሞቅ ነበር።


ከዚህ በኋላ ኢየሱስ “እንዲሁም ኋለኞች የሆኑ ፊተኞች ፊተኞች የሆኑትም ኋለኞች ይሆናሉ፤” አለ።


ነገር ግን አሁን ፊተኞች የሆኑ ብዙዎች ኋለኞች ይሆናሉ፤ ኋለኞች የሆኑትም ፊተኞች ይሆናሉ።”


ጲላጦስም “እንዴት እንዲህ በቶሎ ሞተ?” ብሎ ተደነቀ። የመቶ አለቃውንም አስጠርቶ፥ “በእርግጥ ከሞተ ቈይቶአልን?” ሲል ጠየቀው።


የአይሁድ ከተማ በሆነችው በአርማትያስ የሚኖር ዮሴፍ የሚባል ሰው ነበረ፤ እርሱ ጻድቅና ደግ ሰው ነበረ፤ የአይሁድ ሸንጎ አባልም ነበረ።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios