ዳዊት ሕዝቡን ከቆጠረ በኋላ ኅሊናው ወቀሰው፤ ዳዊትም ጌታን፥ “ባደረግሁት ነገር የፈጸምኩት ታላቅ ኃጢአት ነው፤ አሁን ግን፥ ጌታ ሆይ፤ የአገልጋይህን በደል ይቅር እንድትል እለምንሃለሁ፤ የፈጸምኩት ታላቅ የሞኝነት ሥራ ነውና” አለ።
ማርቆስ 14:72 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ወዲያውም ዶሮ ሁለተኛ ጮኸ። ጴጥሮስም፥ “ዶሮ ሁለት ጊዜ ከመጮኹ በፊት ሦስት ጊዜ ትክደኛለህ” ያለው የኢየሱስ ቃል ትዝ አለው። ከዚያም ስቅስቅ ብሎ አለቀሰ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ወዲያውም ዶሮ ሁለተኛ ጮኸ። ጴጥሮስም፣ “ዶሮ ሁለት ጊዜ ከመጮኹ በፊት ሦስት ጊዜ ትክደኛለህ” ያለው የኢየሱስ ቃል ትዝ አለው። ከዚያም ስቅስቅ ብሎ አለቀሰ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ወዲያውኑ ዶሮ ሁለተኛ ጊዜ ጮኸ፤ ጴጥሮስም “ዶሮ ሁለት ጊዜ ሳይጮኽ፥ ሦስት ጊዜ ትክደኛለህ፤” ሲል ኢየሱስ የተናገረው ቃል ትዝ አለውና ምርር ብሎ አለቀሰ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ጴጥሮስንም ኢየሱስ “ዶሮ ሁለት ጊዜ ሳይጮኽ ሦስት ጊዜ ትክደኛለህ፤” ያለው ቃል ትዝ አለው፤ ነገሩንም አስቦ አለቀሰ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ጴጥሮስንም ኢየሱስ፦ ዶሮ ሁለት ጊዜ ሳይጮኽ ሦስት ጊዜ ትክደኛለህ ያለው ቃል ትዝ አለው፤ ነገሩንም አስቦ አለቀሰ። |
ዳዊት ሕዝቡን ከቆጠረ በኋላ ኅሊናው ወቀሰው፤ ዳዊትም ጌታን፥ “ባደረግሁት ነገር የፈጸምኩት ታላቅ ኃጢአት ነው፤ አሁን ግን፥ ጌታ ሆይ፤ የአገልጋይህን በደል ይቅር እንድትል እለምንሃለሁ፤ የፈጸምኩት ታላቅ የሞኝነት ሥራ ነውና” አለ።
ያደረግሽውን ሁሉ ይቅር ባልሁሽ ጊዜ፥ እንድታስቢውና እንድታፍሪ፥ ከውርደትሽም የተነሣ ደግሞ አፍሽን እንዳትከፍቺ ነው፥ ይላል ጌታ እግዚአብሔር።