ነገር ግን ለድኾች በጽድቅ ይፈርዳል፤ ለምድር ምስኪኖችም ፍትሕን ይበይናል፤ በአፉ በትር ምድርን ይመታል፥ በከንፈሩም እስትንፋስ ክፉዎችን ይገድላል።
ሉቃስ 12:49 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) “በምድር ላይ እሳትን ልጥል መጣሁ፤ አሁን ቢቀጣጠል ምንኛ በወደድሁ? አዲሱ መደበኛ ትርጒም “እኔ የመጣሁት በምድር ላይ እሳት ለመለኰስ ነው፤ አሁኑኑ ቢቀጣጠል ምንኛ ደስ ባለኝ! አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ቀጥሎም ኢየሱስ እንዲህ አለ፦ “እነሆ! እኔ በምድር ላይ እሳት አምጥቻለሁ፤ ታዲያ፥ ቶሎ ቢቀጣጠልልኝ እንዴት በወደድኩ ነበር! የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) “በምድር ላይ እሳትን አምጥቼአለሁ፤ እርስዋን ከማንደድ በቀር ምን እሻለሁ? መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በምድር ላይ እሳት ልጥል መጣሁ፥ አሁንም የነደደ ከሆነ ዘንድ ምን እፈልጋለሁ? |
ነገር ግን ለድኾች በጽድቅ ይፈርዳል፤ ለምድር ምስኪኖችም ፍትሕን ይበይናል፤ በአፉ በትር ምድርን ይመታል፥ በከንፈሩም እስትንፋስ ክፉዎችን ይገድላል።
“እነሆ፥ እንደ ምድጃ እሳት የሚነድ ቀን ይመጣል፤ ትዕቢተኞች ሁሉና ኃጢአትን የሚሠሩ ሁሉ ገለባ ይሆናሉ፤ የሚመጣውም ቀን ያቃጥላቸዋል” ይላል የሠራዊት ጌታ፤ ሥርንና ቅርንጫፍንም አያስቀርላቸውም።
ያላወቀ ግን መገረፍ የሚገባውንም ያደረገ ጥቂት ይገረፋል። ብዙም ከተሰጠው ሰው ሁሉ ከእርሱ ብዙ ይፈለግበታል፤ ብዙ አደራም ከተሰጠው ከእርሱ አብዝተው ይሹበታል።