ዘካርያስም ባየው ጊዜ ደነገጠ፤ በፍርሃትም ተዋጠ።
ዘካርያስም ባየው ጊዜ ደነገጠ፤ በፍርሀትም ተዋጠ።
ዘካርያስ መልአኩን ባየው ጊዜ ደንግጦ በፍርሃት ተዋጠ።
ዘካርያስም ባየው ጊዜ ደነገጠ፤ ፍርሀትም ረዓድም ወረደበት።
ዘካርያስም ባየው ጊዜ ደነገጠ፥ ፍርሃትም ወደቀበት።
ወደ መቃብሩ እንደ ገቡም፥ ነጭ ልብስ የለበሰ ጐልማሳ በቀኝ በኩል ተቀምጦ አዩና ደነገጡ።
እርሷም በንግግሩ በጣም ደንግጣ፥ “ይህ እንዴት ያለ ሰላምታ ይሆን?” ብላ አሰበች።
እርሱም ትኩር ብሎ ሲመለከተው ደንግጦ “ጌታ ሆይ! ምንድነው?” አለ። መልአኩም አለው “ጸሎትህና ምጽዋትህ በእግዚአብሔር ፊት ለመታሰቢያ እንዲሆን አረገ።
ባየሁትም ጊዜ እንደ ሞተ ሰው ሆኜ ከእግሩ በታች ወደቅሁ። ቀኝ እጁንም ጫነብኝ፤ እንዲህም አለኝ “አትፍራ፤ ፊተኛውና መጨረሻው እኔ ነኝ፤
ሚስቱንም፥ “እግዚአብሔርን ስላየን ያለ ጥርጥር እንሞታለን” አላት።
ጌዴዎን ያየው የጌታ መልአክ መሆኑን ባወቀ ጊዜ፥ “ጌታ እግዚአብሔር ሆይ፤ የጌታን መልአክ ፊት ለፊት አይቻለሁና ወዮልኝ” አለ።