ዘሌዋውያን 9:19 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የበሬውንና የአውራውንም በግ ስብ፥ ላቱንም፥ የሆድ ዕቃውንም የሚሸፍነውን ስብ፥ ኩላሊቶቹንም፥ በጉበቱም ላይ ያለውን መረብ አመጡለት። አዲሱ መደበኛ ትርጒም የበሬውንና የአውራ በጉን ሥብ፦ ላቱን፣ የሆድ ዕቃውን የሚሸፍነውን ሥብ፤ ኵላሊቶቹንና የጕበቱን ሽፋን፣ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም አሮንም የወይፈኑንና የበግ አውራውን ስብ ሁሉ ማለትም ላቱን፥ ሆድ ዕቃውን የሚሸፍነውን ስብ፥ እንደ መረብ ሆኖ ጒበቱን የሚሸፍነውን ስብ ምርጥ የሆነውን ክፍል፥ ኲላሊቶቹንና በእነርሱ ላይ ያለውን ስብ ወስዶ፥ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የበሬውንና የአውራውንም በግ ስብ፥ ላቱንም፥ የሆድ ዕቃውንም የሚሸፍነውን ስብ፥ ሁለቱን ኵላሊቶቹንም፥ በላያቸውም ያለውን ስብ፥ የጉበቱንም መረብ አመጡለት። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የበሬውንና የአውራውንም በግ ስብ፥ ላቱንም፥ የሆድ ዕቃውንም የሚሸፍነውን ስብ፥ ኵላሊቶቹንም፥ የጕበቱንም መረብ አመጡለት። |
የሆድ ዕቃውን የሚሸፍነውን ስብ ሁሉ፥ በጉበቱ ላይ ያለውን መረብ፥ ሁለቱን ኩላሊቶችና በላያቸው ያለውን ስብ ወስደህ በመሠዊያው ላይ ታቃጥላለህ።
የአሮንም ልጆች ከሚቃጠል መሥዋዕት ጋር በመሠዊያው ላይ በእሳቱ ላይ ባለው በእንጨቱ ላይ ያቃጥሉታል፤ ለጌታ መዓዛው ያማረ ሽታ የሆነ በእሳት የሚቀርብ ቁርባን ነው።
ከሰላሙም መሥዋዕት ለጌታ በእሳት የሚቀርብ ቁርባን አድርጎ የሚያቀርበው፤ ስቡን፥ እስከ ጀርባውም ድረስ የተቈረጠ ላቱን ሁሉ፥ የሆድ ዕቃውንም የሚሸፍነውን ስብ፥ በሆድ ዕቃውም ላይ ያለውን ስብ ሁሉ፥