ዘሌዋውያን 8:6 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ሙሴም አሮንንና ልጆቹን አቀረበ፥ በውኃም አጠባቸው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ሙሴም አሮንንና ልጆቹን ወደ ፊት አወጣቸው፤ በውሃም ዐጠባቸው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ሙሴም አሮንንና ወንዶች ልጆቹን አቅርቦ በውሃ አጠባቸው፤ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ሙሴም አሮንንና ልጆቹን አቀረበ፤ በውኃም አጠባቸው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ሙሴም አሮንንና ልጆቹን አቀረበ፥ በውኃም አጠባቸው። |
ወደ መገናኛው ድንኳን በሚገቡበት ጊዜ ወይም ለጌታ የእሳት መሥዋዕት ሊያቃጥሉ ወደ መሠዊያው ለማገልገል በሚቀርቡበት ጊዜ እንዳይሞቱ በውኃ ይታጠቡ።
የተቀደሰውን የበፍታ ቀሚስ ይልበስ፥ የበፍታውም ሱሪ በገላው ላይ ይሁን፥ በመርገፍም የተጌጠውን የበፍታው መታጠቂያ ይታጠቅ፥ የበፍታውንም መጠምጠሚያ ይጠምጥም፤ እነዚህ የተቀደሱ ልብሶች ናቸው፤ ገላውንም በውኃ ታጥቦ ይልበሳቸው።
ከእናንተም አንዳንዶቹ እንደ እነዚህ ነበራችሁ፤ ነገር ግን በጌታ በኢየሱስ ክርስቶስ ስም በአምላካችንም መንፈስ ታጥባችኋል፤ ተቀድሳችኋል፤ ጸድቃችኋል።
ነገር ግን ስለ ምግብና ስለ መጠጥም ስለ ልዩ ልዩ የመንጻት ሥርዓቶች የሚውሉ የሥጋ ሥርዓቶች ብቻ ስለ ሆኑ፥ እስከ መታደስ ዘመን ድረስ የተደረጉ ናቸው።
እኔም “ጌታ ሆይ! አንተ ታውቃለህ፤” አልሁት። እንዲህም አለኝም፦ “እነዚህ ከታላቁ መከራ የመጡ ናቸው፤ ልብሶቻቸውንም አጥበው በበጉ ደም አንጽተዋል።