ዘሌዋውያን 8:36 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) አሮንና ልጆቹም ጌታ በሙሴ አንደበት ያዘዘውን ቃላት ሁሉ አደረጉ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም አሮንና ልጆቹም እግዚአብሔር በሙሴ አማካይነት ያዘዘውን ሁሉ አደረጉ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም አሮንና ልጆቹም በሙሴ አማካይነት እግዚአብሔር ያዘዘውን ሁሉ ፈጸሙ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) አሮንና ልጆቹም እግዚአብሔር ለሙሴ ያዘዘውን ሁሉ አደረጉ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) አሮንና ልጆቹም እግዚአብሔር በሙሴ እጅ ያዘዘውን ሁሉ አደረጉ። |
ጌታም ሙሴን እንዳዘዘው በራሱ ላይ መጠምጠሚያውን አደረገ፤ በመጠምጠሚያውም ላይ በፊቱ በኩል፥ የወርቅ ጉንጉን ሆኖ በቅጠል መልክ የተሠራውን የተቀደሰ አክሊል፥ አደረገ።
ሳሙኤልም፦ “ጌታ ለቃሉ በመታዘዝ ደስ የሚለውን ያህል፥ ጌታ፥ በሚቃጠል ቁርባንና መሥዋዕት ደስ ይለዋልን? እነሆ! መታዘዝ ከመሥዋዕት፥ ማዳመጥም ከአውራ በግ ሥብ ይበልጣል።