ዘሌዋውያን 8:10 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ሙሴም የቅባቱን ዘይት ወሰደ፥ ማደሪያውንና በውስጡ ያለውን ሁሉ ቀብቶ ቀደሳቸው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ሙሴም መቅቢያ ዘይቱን ወሰደ፤ ማደሪያ ድንኳኑንና በውስጡ የሚገኘውን ሁሉ ቀብቶ ቀደሰ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከዚህም ቀጥሎ ሙሴ የቅባቱን ዘይት ወስዶ የተቀደሰውን ድንኳንና በውስጡ ያሉትንም ነገሮች ቀባ፤ በዚህ ዐይነት ሁሉንም ለእግዚአብሔር አገልግሎት የተለየ እንዲሆን አደረገው፤ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ሙሴም የቅብዐቱን ዘይት ወሰደ፤ ከእርሱም በመሠዊያው ላይ ሰባት ጊዜ ረጨ፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ሙሴም የቅብዓቱን ዘይት ወሰደ፥ ማደሪያውንና በውስጡ ያለውን ሁሉ ቀብቶ ቀደሳቸው። |
“አሮንን፥ ከእርሱም ጋር ልጆቹን፥ ልብሱንም፥ የቅባቱንም ዘይት፥ ለኃጢአት መሥዋዕትም የሚቀርበውን ወይፈን፥ ሁለቱንም አውራ በጎች፥ እርሾ ያልነካው ቂጣ የሚቀመጥበትንም መሶብ ውሰድ፤