ዘሌዋውያን 7:9 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በምድጃ ላይ የተጋገረው፥ በመጥበሻም ወይም በምጣድ ላይ የተዘጋጀው የእህል ቁርባን ሁሉ ለሚያቀርበው ካህን ይሆናል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም በማብሰያ ምድጃ የተጋገረ፣ በመቀቀያ ወይም በምጣድ የበሰለ ማንኛውም የእህል ቍርባን ለሚያቀርበው ካህን ይሰጥ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በእቶን የተጋገረው የእህል መባ ሁሉ፥ ወይም በመቀቀያ የበሰለውና በምጣድ የተጋገረው መሥዋዕት አድርጎ ላቀረበው ካህን ይሰጣል፤ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በእቶን የተጋገረው የእህል ቍርባን ሁሉ፥ በመቀቀያም ወይም በምጣድ የበሰለው ሁሉ ለሚያቀርበው ካህን ይሆናል። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በእቶን የተጋገረው የእህል ቍርባን ሁሉ፥ በመቀቀያም ወይም በምጣድ የበሰለው ሁሉ ለሚያቀርበው ካህን ይሆናል። |
ካህኑም ከእነዚያ በአንዳቸው ስለ ሠራው ኃጢአት ያስተሰርይለታል፥ እርሱም ይቅር ይባላል። እንደ እህል ቁርባንም እንዲሁ የተረፈው ለካህኑ ይሆናል።”
በእሳት ከሚቀርበው እጅግ ከተቀደሰው ይህ ለአንተ ይሆናል፤ ለእኔ የሚያመጡት መባቸው ሁሉ፥ የእህሉ ቁርባናቸው ሁሉ፥ የኃጢአታቸውም መሥዋዕት ሁሉ፥ የበደላቸውም መሥዋዕት ሁሉ፥ ለአንተ ለልጆችህም እጅግ የተቀደሰ ይሆናል።
ከቶ በገዛ ገንዘቡ በወታደርነት የሚያገለግል ማን ነው? ወይን ተክሎ ፍሬውን የማይበላ ማን ነው? ወይስ መንጋ እየጠበቀ ከመንጋው ወተት የማይጠጣ ማን ነው?