ፅኑ ፍቅሩን እስከ ሺህ ትውልድ የሚጠብቅ፥ አበሳን፥ መተላለፍንና ኃጢአትን ይቅር የሚል፥ በደለኛውን ከቶ የማያነጻ፥ የአባቶችን ኃጢአት በልጆችና በልጅ ልጆች ላይ እስከ ሦስትና እስከ አራት ትውልድ የሚያመጣ አምላክ ነው።”
ዘሌዋውያን 6:7 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ካህኑም በጌታ ፊት ያስተሰርይለታል፥ ስለዚያም ስላደረገው በደል ሁሉ ይቅር ይባላል።” አዲሱ መደበኛ ትርጒም በዚህም ሁኔታ ካህኑ በእግዚአብሔር ፊት ያስተሰርይለታል፤ ሰውየውም ስለ ፈጸመው ስለ ማንኛውም በደል ይቅር ይባላል።” አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ካህኑም ስለዚያ ሰው ኃጢአት ማስተስረያ በእግዚአብሔር ፊት መሥዋዕቱን ያቅርብ፤ በደለኛ ከሆነበት ጉዳይ ሁሉ ኃጢአቱ ይቅር ይባልለታል።” የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ካህኑም በእግዚአብሔር ፊት ያስተሰርይለታል፤ ስለዚያም ስለ አደረገው በደል ሁሉ ይቅር ይባልለታል።” መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ካህኑም በእግዚአብሔር ፊት ያስተሰርይለታል፥ ስለዚያም ስላደረገው በደል ሁሉ ይቅር ይባላል። |
ፅኑ ፍቅሩን እስከ ሺህ ትውልድ የሚጠብቅ፥ አበሳን፥ መተላለፍንና ኃጢአትን ይቅር የሚል፥ በደለኛውን ከቶ የማያነጻ፥ የአባቶችን ኃጢአት በልጆችና በልጅ ልጆች ላይ እስከ ሦስትና እስከ አራት ትውልድ የሚያመጣ አምላክ ነው።”
የኃጢአት መሥዋዕት በሆነው ወይፈን ላይ እንዳደረገው እንዲሁ በዚህ ወይፈን ላይ ደግሞ ያደርጋል፤ እርሱም እንዲህ ያደርግበታል፤ ካህኑም ስለ እነርሱ ያስተሰርያል፥ እነርሱም ይቅር ይባላሉ።
ከአንድነት መሥዋዕት ላይ እንደተወሰደው ስብ እንዲሁ የእርሷን ስብ ሁሉ ይወስዳል፤ ካህኑም ለጌታ መዓዛው ያማረ ሽታ እንዲሆን በመሠዊያው ላይ ያቃጥለዋል፤ ካህኑም ስለ እርሱ ያስተሰርያል፥ እርሱም ይቅር ይባላል።
ካህኑም ከእነዚያ በአንዳቸው ስለ ሠራው ኃጢአት ያስተሰርይለታል፥ እርሱም ይቅር ይባላል። እንደ እህል ቁርባንም እንዲሁ የተረፈው ለካህኑ ይሆናል።”
ነውር የሌለበትን አውራ በግ ከመንጋው እንደ ግምጋሜህ መጠን ለበደል መሥዋዕት ወደ ካህኑ ያመጣል፤ ካህኑም ሳያውቅ ስለ ሠራው ስሕተት ያስተሰርይለታል፥ እርሱም ይቅር ይባላል።
በደልን ይቅር የሚል፥ የርስቱን ትሩፍ ዓመጽ የሚያሳልፍ እንደ አንተ ያለ አምላክ ማን ነው? ርኅራኄ ይወድዳልና ቁጣውን ለዘለዓለም አያቆይም።
ነገር ግን እርሱ በብርሃን እንዳለ በብርሃን ብንመላለስ እርስ በእርሳችን ኅብረት አለን፥ የልጁም የኢየሱስ ክርስቶስ ደም ከኃጢአት ሁሉ ያነጻናል።