የኃጢአት መሥዋዕት በሆነው ወይፈን ላይ እንዳደረገው እንዲሁ በዚህ ወይፈን ላይ ደግሞ ያደርጋል፤ እርሱም እንዲህ ያደርግበታል፤ ካህኑም ስለ እነርሱ ያስተሰርያል፥ እነርሱም ይቅር ይባላሉ።
ዘሌዋውያን 5:10 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እንደ ሥርዓቱም ሁለተኛውን ለሚቃጠል መሥዋዕት ያዘጋጀዋል። ካህኑም ስለ ሠራው ኃጢአት ያስተሰርይለታል፥ እርሱም ይቅር ይባላል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ካህኑም ቀደም ሲል በታዘዘው መሠረት ሁለተኛዋን የሚቃጠል መሥዋዕት አድርጎ ያቅርብ፤ ካህኑም የሰውየውን ኀጢአት ያስተሰርይለታል፤ ሰውየውም ይቅር ይባላል። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ሌላይቱንም በሥርዓቱ መሠረት የሚቃጠል መሥዋዕት አድርጎ ያቅርብ፤ በዚህም ዐይነት ካህኑ ስለ ኃጢአት የሚሠዋውን መሥዋዕት ያቀርባል፤ በደል የሠራውም ሰው ኃጢአቱ ይቅር ይባልለታል። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እንደ ሥርዐቱም ሁለተኛውን ለሚቃጠል መሥዋዕት ያዘጋጀዋል። ካህኑም ስለ ሠራው ኀጢአት ያስተሰርይለታል፤ ኀጢአቱም ይሰረይለታል። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እንደ ሥርዓቱም ሁለተኛውን ለሚቃጠል መሥዋዕት ያዘጋጀዋል። ካህኑም ስለ ሠራው ኃጢአት ያስተሰርይለታል፥ እርሱም ይቅር ይባላል። |
የኃጢአት መሥዋዕት በሆነው ወይፈን ላይ እንዳደረገው እንዲሁ በዚህ ወይፈን ላይ ደግሞ ያደርጋል፤ እርሱም እንዲህ ያደርግበታል፤ ካህኑም ስለ እነርሱ ያስተሰርያል፥ እነርሱም ይቅር ይባላሉ።
ከአንድነት መሥዋዕት ላይ እንደተወሰደው ስብ እንዲሁ የእርሷን ስብ ሁሉ ይወስዳል፤ ካህኑም ለጌታ መዓዛው ያማረ ሽታ እንዲሆን በመሠዊያው ላይ ያቃጥለዋል፤ ካህኑም ስለ እርሱ ያስተሰርያል፥ እርሱም ይቅር ይባላል።
ለአንድነት መሥዋዕት ከሚቀርበው ጠቦት ላይ ስቡ እንደሚወሰድ እንዲሁ የእርሷን ስብ ሁሉ ይወስዳል፤ ካህኑም ለጌታ በእሳት ከሚቀርበው ቁርባን ጋር በመሠዊያው ላይ ያቃጥለዋል። ካህኑም ስለ ሠራው ኃጢአት ያስተሰርይለታል፥ እርሱም ይቅር ይባላል።
ካህኑም ከእነዚያ በአንዳቸው ስለ ሠራው ኃጢአት ያስተሰርይለታል፥ እርሱም ይቅር ይባላል። እንደ እህል ቁርባንም እንዲሁ የተረፈው ለካህኑ ይሆናል።”
በተቀደሰ ነገር ላይ ስለ ሠራው ኃጢአት ዕዳ ይከፍላል፥ በሚከፍለውም ዕዳ ላይ አምስት እጅ ይጨምርበታል፥ ለካህኑም ይሰጠዋል። ካህኑም በበደል መሥዋዕት አውራ በግ ያስተሰርይለታል፥ እርሱም ይቅር ይባላል።
ስለ ሠራው ኃጢአት ለጌታ የበደል መሥዋዕት ያመጣል፤ እርሱም ከመንጋው የበግ ወይም የፍየል እንስት ለኃጢአት መሥዋዕት ያቀርባል፤ ካህኑም ስለ ኃጢአቱ ያስተሰርይለታል።
ክርስቶስም እንዳፈቀራችሁ፥ ስለ እናንተም ለእግዚአብሔር መልካም መዓዛ ያለው መባንና መሥዋዕት አድርጎ ራሱን አሳልፎ እንደሰጠ፥ በፍቅር ተመላለሱ።