La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




ዘሌዋውያን 4:10 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

ለአንድነት መሥዋዕት ከሚቀርበው ወይፈን እንደሚወሰደው ከወሰደ በኋላ፥ ካህኑ የሚቃጠል መሥዋዕት በሚቀርብበት መሠዊያ ላይ ያቃጥለዋል።

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

ለኅብረት መሥዋዕት ከሚቀርበው ወይፈን እንዳወጣ ሁሉ ሥቡን ያውጣ፤ ካህኑም የሚቃጠል መሥዋዕት በሚቀርብበት መሠዊያ ላይ ያቃጥለው።

Ver Capítulo

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

ሊቀ ካህናቱም ይህን ስብ ሁሉ ተቀብሎ የሚቃጠል መሥዋዕት በሚቀርብበት መሠዊያ ላይ ያቃጥለው፤ አፈጻጸሙም ለአንድነት መሥዋዕት ከሚቀርበው የእንስሳ ስብ ወስዶ ለሚቃጠል መሥዋዕት በሚያቀርበው ዐይነት ይሁን።

Ver Capítulo

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

ለደ​ኅ​ን​ነት መሥ​ዋ​ዕት ከታ​ረ​ደው ወይ​ፈን እንደ ተወ​ሰ​ደው ይወ​ስ​ዳል፤ ካህ​ኑም ለሚ​ቃ​ጠል መሥ​ዋ​ዕት በሚ​ሆ​ነው መሠ​ዊያ ላይ ያቀ​ር​በ​ዋል።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

ለደኅንነት መሥዋዕት ከታረደው ወይፈን እንደ ተወሰደው ይወስዳል። ካህኑም ለሚቃጠል መሥዋዕት በሚሆነው መሠዊያ ላይ ያቃጥለዋል።

Ver Capítulo



ዘሌዋውያን 4:10
3 Referencias Cruzadas  

ከሰላሙም መሥዋዕት ለጌታ በእሳት የሚቀርብ ቁርባን አድርጎ የሚያቀርበው፤ የሆድ ዕቃውን የሚሸፍነውን ስብ፥ በሆድ ዕቃውም ላይ ያለውን ስብ ሁሉ፥


የወይፈኑን ቆዳ፥ ሥጋውንም ሁሉ፥ ራሱንም፥ እግሮቹንም፥ ሆድ ዕቃውንም፥ ፈርሱንም፥


ሁለቱንም ኩላሊቶች፥ በእነርሱም ላይና በጎድኑ አጠገብ ያለውን ስብ፥ በጉበቱም ላይ ያለውን መረብ ከኩላሊቶች ጋር፥