የምድያም ነጋዶችም አለፉ፥ እነርሱም ዮሴፍን አንሥተው ከጉድጓድ አወጡት፥ ለእስማኤላውያንም ዮሴፍን በሃያ ብር ሸጡት፥ እነርሱም ዮሴፍን ወደ ግብጽ ወሰዱት።
ዘሌዋውያን 27:5 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ከአምስት ዓመትም ጀምሮ እስከ ሀያ ዓመት ድረስ ግምትህ ለወንድ ሀያ ሰቅል፥ ለሴትም ዐሥር ሰቅል ይሁን። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ዕድሜው ከዐምስት እስከ ሃያ ዓመት ለሆነ ሰው፣ ወንድ ከሆነ ግምቱ ሃያ ሰቅል፣ ሴት ከሆነች ግምቷ ዐሥር ሰቅል ይሁን። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከአምስት እስከ ኻያ ዓመት ለሆነው ወንድ ኻያ ጥሬ ብር ይሁን፤ በዚሁ ዕድሜ ክልል ላለች ሴት ዐሥር ጥሬ ብር ይሁን፤ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ከአምስት ዓመትም ጀምሮ እስከ ሃያ ዓመት ድረስ ግምቱ ለወንድ ሃያ የብር ዲድርክም፥ ለሴትም ዐሥር የብር ዲድርክም ይሁን። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ከአምስት ዓመትም ጀምሮ እስከ ሀያ ዓመት ድረስ ግምቱ ለወንድ ሀያ ሰቅል፥ ለሴትም አሥር ሰቅል ይሁን። |
የምድያም ነጋዶችም አለፉ፥ እነርሱም ዮሴፍን አንሥተው ከጉድጓድ አወጡት፥ ለእስማኤላውያንም ዮሴፍን በሃያ ብር ሸጡት፥ እነርሱም ዮሴፍን ወደ ግብጽ ወሰዱት።