ኢዮአስም ካህናቱን ጠርቶ በቤተ መቅደስ ከሚቀርበው መሥዋዕት ጋር ግንኙነት ባለው ሁኔታ መባ ሆኖ የሚገባውን ገንዘብ ሁሉ በጥንቃቄ እንዲጠብቁ አዘዘ፤ ይኸውም ቋሚ ከሆነው ከዘወትር መሥዋዕት ጋር መባ ሆኖ የሚቀርበውንና በበጎ ፈቃድ ሕዝቡ የሚያመጣውን ስጦታ ሁሉ የሚያጠቃልል ነበር።
ዘሌዋውያን 27:3 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ለወንድ ከሃያ ዓመት ጀምሮ እስከ ስልሳ ዓመት ድረስ እንደ መቅደሱ ሰቅል ሚዛን ግምትህ ኀምሳ የብር ሰቅል ይሁን። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ዕድሜው ከሃያ እስከ ስድሳ ዓመት ለሆነ ወንድ፣ በቤተ መቅደሱ ሰቅል ሚዛን መሠረት፣ ግምቱ ዐምሳ ጥሬ ሰቅል ብር ይሁን። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በቤተ መቅደሱስ በታወቀው ሚዛን ልክ ዕድሜው ከኻያ እስከ ሥልሳ ለሆነ ወንድ 600 ግራም የሚመዝን ጥሬ ብር ይሁን፤ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ለወንድ ከሃያ ዓመት ጀምሮ እስከ ስድሳ ዓመት ድረስ እንደ መቅደሱ ሚዛን ግምቱ አምሳ የብር ዲድርክም ይሁን። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ለወንድ ከሃያ ዓመት ጀምሮ እስከ ስድሳ ዓመት ድረስ እንደ መቅደሱ ሰቅል ሚዛን ግምቱ አምሳ የብር ሰቅል ይሁን። |
ኢዮአስም ካህናቱን ጠርቶ በቤተ መቅደስ ከሚቀርበው መሥዋዕት ጋር ግንኙነት ባለው ሁኔታ መባ ሆኖ የሚገባውን ገንዘብ ሁሉ በጥንቃቄ እንዲጠብቁ አዘዘ፤ ይኸውም ቋሚ ከሆነው ከዘወትር መሥዋዕት ጋር መባ ሆኖ የሚቀርበውንና በበጎ ፈቃድ ሕዝቡ የሚያመጣውን ስጦታ ሁሉ የሚያጠቃልል ነበር።
በቆጠራው የሚያልፉ ሁሉ ይህን ይስጡ፥ በመቅደሱ ሰቅል ሚዛን መሠረት ግማሽ ሰቅል ይሰጣል፥ ሰቅል ሃያ ጌራ ነው፤ ግማሽ ሰቅል ለጌታ ስጦታ ነው።
ለመቅደሱ ሥራ የተደረገው ወርቅ ሁሉ፥ የተሰጠው ወርቅ በሙሉ፥ በመቅደሱ ሰቅል ሚዛን መሠረት ሀያ ዘጠኝ መክሊት ሰባት መቶ ሠላሳ ሰቅል ነበረ።
“ለጌታም ቅዱስ ይሆን ዘንድ ሰው ቤቱን ቢቀድስ፥ ካህኑ መልካም ወይም መጥፎ እንደሆነ ይገምተዋል፤ ካህኑም እንደሚገምተው መጠን እንዲሁ ይጸናል።
“ማናቸውም ሰው ቢተላለፍ፥ ሳያውቅም ለጌታ በተቀደሰው በማናቸውም ነገር ኃጢአትን ቢሠራ፥ ለበደል መሥዋዕት ለጌታ ከመንጋው ነውር የሌለበትን አውራ በግ ያመጣል፤ ተመጣጣኝ የሆነ ዋጋ በብር ሰቅል እንደ መቅደሱ ሰቅል ሚዛን ለበደል መሥዋዕት ያቀርበዋል።
ከአንድ ወር ጀምሮ የምትዋጀውን እንደ ግምትህ ትዋጀዋለህ፤ ግምቱም እንደ መቅደሱ ሰቅል ሚዛን አምስት ሰቅል ይሆናል፤ እርሱም ሀያ አቦሊ ነው።