ዘሌዋውያን 27:26 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) “ዳሩ ግን ለጌታ የሆነውን የእንስሳ በኵራት ማንም ሰው ሊቀድሰው አይችልም፤ በሬ ቢሆን ወይም በግ ለጌታ ነው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም “ ‘የእንስሳት በኵር ቀድሞውኑ የእግዚአብሔር ስለ ሆነ፣ ማንም ሰው የእንስሳትን በኵር ለእግዚአብሔር መቀደስ አይችልም፤ በሬም ሆነ በግ የእግዚአብሔር ነውና። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም “በኲር ሆኖ የሚወለድ እንስሳ ቀድሞውኑ የእግዚአብሔር ስለ ሆነ ማንም ሰው የበጎ ፈቃድ ስጦታ አድርጎ ሊያቀርበው አይችልም፤ እንቦሳም ሆነ የበግና የፍየል ግልገሎች አስቀድመው ለእግዚአብሔር የተለዩ ናቸው፤ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) “ከእንስሳህ የሚወለድ በኵር ሁሉ ለእግዚአብሔር ነው፤ ማንም ይለውጠው ዘንድ አይቻለውም፤ በሬ ቢሆን ወይም በግ ለእግዚአብሔር ነው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ለእግዚአብሔር ግን የሚቀርበውን የእንስሳ በኵራት ማንም ይቀድሰው ዘንድ አይቻለውም፤ በሬ ቢሆን ወይም በግ ለእግዚአብሔር ነው። |
በሕጉም እንደ ተጻፈ የልጆቻችንና የእንስሶቻችንን በኵራት፥ የበሬዎቻችንንና የበጎቻችንን በኵራት፥ በአምላካችን ቤት ወደ ሚያገለግሉት ካህናት ወደ አምላካችን ቤት እናመጣ ዘንድ፥
ነገር ግን የላም በኵራት ወይም የበግ በኵራት ወይም የፍየል በኵራት አትዋጅም፤ የተቀደሱ ናቸው፤ ደማቸውን በመሠዊያው ላይ እርጨው፥ ስባቸውንም ለጌታ መዓዛው ያማረ ሽታ እንዲሆን በእሳት የሚቀርብ ቁርባን አድርገህ አቃጥለው።
ምክንያቱም በኩር ሁሉ የእኔ ነውና፤ በግብጽ ምድር በኩርን ሁሉ በገደልሁ ቀን፥ ከእስራኤል ዘንድ በኩርን ሁሉ፥ ከሰው ጀምሮ እስከ እንስሳ ድረስ ያለውን ለእኔ ለይቼአለሁ፤ ለእኔ ይሆናሉ። እኔ ጌታ ነኝ።”
“የቀንድ ከብት፥ የበግና የፍየል መንጋዎችህን ተባዕት በኩር ሁሉ ለጌታ ለእግዚአብሔር ትቀድሳለህ። የበሬህን በኩር አትሥራበት፤ የበግህንም በኩር አትሸልት፤