ዘሌዋውያን 26:15 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ሥርዓቴንም ባትቀበሉ፥ ነፍሳችሁም ፍርዴን በመጸየፉዋ ምክንያት ትእዛዛቴን ሳታደርጉ ቃል ኪዳኔን ብታፈርሱ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም ሥርዐቴን ብትንቁ፣ ሕጌን ብታቃልሉ፣ ትእዛዞቼንም ሁሉ ባለመፈጸም ቃል ኪዳኔን ብታፈርሱ፣ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ትእዛዞቼን ባትጠብቁ፥ ሕግጋቴን ብትንቁ፥ ቃል ኪዳኔን ብታፈርሱና ሥርዓቶቼን ብትጸየፉ፥ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ሥርዐቴንም ብትንቁ፥ ትእዛዛቴንም ሁሉ እንዳታደርጉ፥ ቃል ኪዳኔንም እንድታፈርሱ ሰውነታችሁ ፍርዴን ብትሰለች፥ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ሥርዓቴንም ብትንቁ፥ ትእዛዛቴንም ሁሉ እንዳታደርጉ፥ ቃል ኪዳኔንም እንድታፈርሱ ነፍሳችሁ ፍርዴን ብትጸየፍ፥ |
የሰጣቸውንም ድንጋጌ አልተቀበሉም፤ ከቀድሞ አባቶቻቸው ጋር የገባውንም ቃል ኪዳን አልጠበቁም፤ የሰጣቸውንም ማስጠንቀቂያዎች ሁሉ ቸል አሉ፤ ለከንቱ ጣዖቶች በመስገድ ራሳቸውም ከንቱዎች ሆኑ፤ የእነርሱን መጥፎ ምሳሌነት እንዳይወርሱ እግዚአብሔር የሰጣቸውን ትእዛዝ በመሻር በዙሪያቸው የሚኖሩ የአሕዛብን ልማድ ሁሉ ተከተሉ።
እነርሱ ግን የጌታ ቁጣ በሕዝቡ ላይ እስኪወርድባቸው ድረስ፥ ፈውስም እስከማይገኝላቸው ድረስ፥ በጌታ መልክተኞች ይሳለቁ፥ ቃላቱንም ያቃልሉ፥ በነቢያቱም ላይ ያፌዙ ነበር።
ቃሌንም ለመስማት እንቢ ወዳሉ ወደ ቀድሞው አባቶቻቸው ኃጢአት ተመለሱ፥ ሊያገለግሉአቸውም እንግዶችን አማልክት ተከተሉ፤ የእስራኤል ቤትና የይሁዳ ቤት ከአባቶቻቸው ጋር ያደረግሁትን ቃል ኪዳን አፈረሱ።
እጃቸውን ይዤ ከግብጽ አገር ባወጣኋቸው ቀን ከአባቶቻቸው ጋር እንደ አደረግሁት ያለ ቃል ኪዳን አይደለም፤ እኔ ገዢአቸው ብሆንም እንኳ ያን ያደረግሁትን ቃል ኪዳን አፍርሰዋል፥ ይላል ጌታ።
ምድርሪቱም በእነርሱ ትተዋለች፤ ያለ እነርሱም ባድማ ሆና እስከተቀመጠችበት ጊዜ ድረስ ሰንበታትን በማድረግዋ ትደሰታለች፤ ፍርዴንም ስላልተቀበሉ፥ ነፍሳቸውም ሥርዓቴን ስለ ተጸየፈች የበደላቸውን ቅጣት ይቀበላሉ።
“ባትሰሙ፥ ለስሜም ክብር ለመስጠት በልባችሁ ባታኖሩት፥” ይላል የሠራዊት ጌታ፥ “እርግማን እልክባችኋለሁ፥ በረከታችሁንም እረግማለሁ፤ አሁንም ረግሜዋለሁ ምክንያቱም በልባችሁ አላደረጋችሁትምና።”
“እናንተ የምትንቁ፥ ተመልከቱ፤ ተደነቁም፤ ጥፉም፤ ማንም ቢተርክላችሁ የማታምኑትን ሥራ በዘመናችሁ እኔ እሠራለሁና፤” ተብሎ በነቢያት የተነገረው እንዳይደርስባችሁ ተጠንቀቁ።
ጌታም ሙሴን እንዲህ አለው፦ “እነሆ፥ ከአባቶችህ ጋር ልታርፍ ነው፤ ይህም ሕዝብ በሚገባበት ምድር በሚገኙ ባዕዳን አማልክት ወዲያውኑ ያመነዝራል። እኔን ይተወኛል፤ ከእነርሱም ጋር የገባሁትን ኪዳን ያፈርሳሉ።
ከግብጽ ምድር ለማውጣት እጃቸውን በያዝሁበት ቀን ከአባቶቻቸው ጋር እንደገባሁት ኪዳን አይደለም፤ እነርሱ በኪዳኔ አልጸኑምና እኔም ቸል አልኳቸው፤ ይላል ጌታ።