ዘሌዋውያን 25:53 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በእርሱ ዘንድ በየዓመቱ እንደሚቀጠር አገልጋይ ይሁን እንጂ በአንተ ፊት በጽኑ እጅ አይግዛው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከዓመት እስከ ዓመት እንደ ቅጥር ሠራተኛ ይኑር፤ አሳዳሪውም በፊትህ በጭካኔ አይግዛው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ይህም መሆን ያለበት በዓመት ክፍያ እንደ ተቀጠረ ሰው ታስቦ ነው፤ ጌታው እርሱን በማስጨነቅ መግዛት የለበትም። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በየዓመቱ እንደ ምንደኛ ከእርሱ ጋር ይኑር፤ በፊትህ እንደ ቀደመው አያስጨንቀው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በየዓመቱ እንደ ምንደኛ ከእርሱ ጋር ይኑር፤ በፊትህ በጽኑ እጅ አይግዛው። |
ከእናንተም በኋላ ልጆቻችሁ ለዘለዓለም እንዲወርሱአቸው ተዉአቸው፤ እነርሱን ባርያዎች ታደርጋላችሁ፥ ነገር ግን የእስራኤል ልጆች ወንድሞቻችሁ ናቸውና አንዱ ሌላውን በጽኑ እጅ አይግዛው።
እስከ ኢዮቤልዩ ዓመት ድረስ ጥቂቶች ዓመታት ቢቀሩ ከእርሱ ጋር በመሆን ያሰላል፤ እርሱ ማገልገል እንደሚገባው የዓመታት መጠን የመቤዠቱን ዋጋ ይመልስ።