ዘሌዋውያን 25:13 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) “በዚህ በኢዮቤልዩ ዓመት እያንዳንዱ ሰው ወደ ርስቱ ይመለሳል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም “ ‘በዚህ በኢዮቤልዩ ዓመት እያንዳንዱ ሰው ወደ ርስቱ ይመለስ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም “ከዚያ በፊት የተሸጠ መሬት ሁሉ በዚሁ ዓመት ለባለቤቱ ይመለስለታል፤ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) “በዚች ኢዮቤልዩ ዓመት ሰው ሁሉ ወደ ርስቱ ይመለሳል። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በዚች በኢዮቤልዩ ዓመት ሰው ሁሉ ወደ ርስቱ ይመለሳል። |
በሕይወት እስካሉ ድረስ ሻጭ ወደሸጠው ነገር አይመለስ፥ ስለ ብዙዎቹ የተነገረው ራእይ አይመለስምና፥ ማንም ሰው በኃጢአቱ ሕይወቱን ማዳን አይችልም።
ኀምሳኛውንም ዓመት ትቀድሳላችሁ፥ በምድሪቱም ለሚኖሩባት ሁሉ ነጻነትን ታውጃላችሁ፤ እርሱ ለእንናተ ኢዮቤልዩ ይሆናል፤ ከእናንተም እያንዳንዱ ሰው ወደ ርስቱና ወደ ወገኑ ይመለሳል።
ለማስመለስ ግን በቂ ገንዘብ ባያገኝ፥ ሽያጩ እስከ ኢዮቤልዩ ዓመት ድረስ በገዛው ሰው እጅ ይሆናል፤ በኢዮቤልዩ ዓመት ነፃ ይወጣል፥ እርሱም ወደ ርስቱ ይመለሳል።
ለእስራኤልም ልጆች ኢዮቤልዩ በመጣ ጊዜ ርስታቸው እነርሱ ወደ አሉበት ነገድ ርስት ይጨመራል፤ ርስታቸውም ከአባቶቻችን ነገድ ርስት ይወሰዳል።”