በመጀመሪያውም ቀን የተቀደሰ ጉባኤ እንዲሁም በሰባተኛውም ቀን የተቀደሰ ጉባኤ ይሆንላችኋል። ለሁሉም ሰው የሚሆን የሚበላ ካልሆነ በቀር በእነርሱ ቀናት ምንም አትሥሩ፥ ይህንም ብቻ ታደርጋላችሁ።
ዘሌዋውያን 23:7 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በመጀመሪያው ቀን የተቀደሰ ጉባኤ ይኑራችሁ፤ የጉልበት ሥራ ሁሉ አትሥሩበት። አዲሱ መደበኛ ትርጒም በመጀመሪያው ቀን የተቀደሰ ጉባኤ አድርጉ፤ የዘወትር ተግባራችሁንም አታከናውኑ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከእነዚህ ዕለቶች በመጀመሪያው ቀን ለአምልኮ ትሰበሰባላችሁ፤ ከዕለት ተግባራችሁ ማንኛውንም በዚህ ቀን አትሠሩም። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) መጀመሪያይቱ ቀን ቅድስት ጉባኤ ትሁንላችሁ፤ የተግባር ሥራ ሁሉ አትሥሩባት። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በመጀመሪያው ቀን የተቀደሰ ጉባኤ ይሁንላችሁ፤ የተግባር ሥራ ሁሉ አትሥሩበት። |
በመጀመሪያውም ቀን የተቀደሰ ጉባኤ እንዲሁም በሰባተኛውም ቀን የተቀደሰ ጉባኤ ይሆንላችኋል። ለሁሉም ሰው የሚሆን የሚበላ ካልሆነ በቀር በእነርሱ ቀናት ምንም አትሥሩ፥ ይህንም ብቻ ታደርጋላችሁ።
በዚያም ቀን ታውጃላችሁ፤ የተቀደሰ ጉባኤም ታደርጋላችሁ። የጉልበት ሥራ ሁሉ አትሥሩበት። በምትቀመጡበት አገር ሁሉ ለልጅ ልጃችሁ የዘለዓለም ሥርዓት ነው።
በሰባተኛውም ወር በዓሥራ አምስተኛው ቀን የተቀደሰ ጉባኤ ይኑራችሁ፤ የጉልበት ሥራ ሁሉ አትሥሩበት፥ ሰባት ቀንም ለጌታ በዓል አድርጋችሁ ታከብራላችሁ።