ዘሌዋውያን 22:32 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እኔም በእስራኤል ልጆች መካከል እንድቀደስ የተቀደሰውን ስሜን አታርክሱ፤ የምቀድሳችሁ እኔ ጌታ ነኝ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ቅዱሱን ስሜን አታርክሱ፤ እኔ ቅዱስ መሆኔ በእስራኤላውያን ዘንድ ይታወቅ፤ የምቀድሳችሁ እኔ እግዚአብሔር ነኝ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የተቀደሰውን ስሜን አታዋርዱ፤ መላው የእስራኤል ሕዝብ እኔ ቅዱስ መሆኔን ተገንዝበው ያክብሩኝ፤ የምቀድሳችሁ እኔ እግዚአብሔር ነኝ፤ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የተቀደሰውንም ስሜን አታርክሱ፤ እኔ ግን በእስራኤል ልጆች መካከል እቀደሳለሁ፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የተቀደሰውንም ስሜን አታርክሱ፤ እኔ ግን በእስራኤል ልጆች መካከል እቀደሳለሁ፤ |
ሙሴም አሮንን፦ “ጌታ፦ ‘ወደ እኔ በሚቀርቡ እቀደሳለሁ፥ በሕዝቡም ሁሉ ፊት እከብራለሁ’ ብሎ የተናገረው ይህ ነው” አለው፤ አሮንም ዝም አለ።
“የተቀደሰውንም ስሜን እንዳያረክሱ፥ የእስራኤል ልጆች ለእኔ ከሚቀድሱአቸው ከቅዱሳን ነገሮች ራሳቸውን እንዲለዩ ለአሮንና ለልጆቹ ተናገር፤ እኔ ጌታ ነኝ።
ኢየሱስም እንዲህ አላቸው፦ “በማናቸውም ጊዜ ስትጸልዩ እንዲህ በሉ፦ ‘በሰማያት የምትኖር አባት ሆይ! ስምህ ይቀደስ፤ መንግሥትህ ትምጣ፤ ፈቃድህ በሰማይ እንደ ሆነች እንዲሁ በምድር ትሁን፤
በቆሮንቶስ ላለች ለእግዚአብሔር ቤተ ክርስቲያን፥ በክርስቶስ ኢየሱስ ለተቀደሱት፥ ቅዱሳን ለመሆን ለተጠሩት፥ የእነርሱና የእኛ ጌታ የሆነውን የጌታችንን የኢየሱስ ክርስቶስን ስም በየስፍራው ከሚጠሩት ሁሉ ጋር፤