ያዕቆብም እንዲህ ብሎ ስእለት ተሳለ፦ “እግዚአብሔር ከእኔ ጋር ቢሆን፥ በምሄድባትም በዚች መንገድ ቢጠብቀኝ፥ የምበላውንም እንጀራ የምለብሰውንም ልብስ ቢሰጠኝ፥
ዘሌዋውያን 22:21 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ማናቸውም ሰው ከበሬ ወይም ከበግ መንጋ ስእለቱን ለመፈጸም ወይም በፈቃዱ ለማቅረብ የአንድነትን መሥዋዕት ለጌታ ቢያቀርብ፥ እንዲሠምርለት ፍጹም የሆነ ይሁን፥ በእርሱም ነውር የሆነ ነገር አይኑርበት። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ማንኛውም ሰው ስእለት ለመፈጸም ወይም የበጎ ፈቃድ ስጦታ ለማበርከት ከላም ወይም ከበግ ወይም ከፍየል መንጋ ለእግዚአብሔር የኅብረት መሥዋዕት ሲያቀርብ፣ ተቀባይነት ይኖረው ዘንድ ፍጹም የሆነውንና እንከን የሌለበትን ያቅርብ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ማንም ሰው ስእለት ተፈጽሞለት ወይም የበጎ ፈቃድ ስጦታ አድርጎ የአንድነት መሥዋዕት ለእግዚአብሔር ቢያቀርብ፥ ተቀባይነት ማግኘት እንዲችል፥ እንስሳው ምንም ነውር የሌለበት ይሁን። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ማናቸውም ሰው ስእለቱን ለመፈጸም ወይም በፈቃዱ ለማቅረብ የደኅንነትን መሥዋዕት፥ ወይም በሬን፥ ወይም በግን፥ ለእግዚአብሔር ቢያቀርብ፥ ይሰምርለት ዘንድ ፍጹም ይሁን፤ ነውርም አይሁንበት። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ማናቸውም ሰው ስእለቱን ለመፈጸም ወይም በፈቃዱ ለማቅረብ የደኅንነትን መሥዋዕት፥ ወይም በሬን ወይም በግን፥ ለእግዚአብሔር ቢያቀርብ፥ ይሠምርለት ዘንድ ፍጹም ይሁን፥ ነውርም አይሁንበት። |
ያዕቆብም እንዲህ ብሎ ስእለት ተሳለ፦ “እግዚአብሔር ከእኔ ጋር ቢሆን፥ በምሄድባትም በዚች መንገድ ቢጠብቀኝ፥ የምበላውንም እንጀራ የምለብሰውንም ልብስ ቢሰጠኝ፥
ከእስራኤል ልጆች ልባቸው ያነሣሣቸው ወንዶችና ሴቶች ሁሉ ጌታ በሙሴ እጅ እንዲሠራ ላዘዘው ሥራ ሁሉ የሚሆን ስጦታ በፈቃዳቸው ለጌታ አመጡ።
ዓይነ ስውር ወይም የተሰበረ ወይም አካለ ጎዶሎ ወይም የሚመግል ቁስል ወይም የእከክ ደዌ ያለበት ወይም ቋቁቻ የወጣበት ቢሆን፥ እነዚህን ሁሉ ለጌታ አታቅርቡ፤ እነርሱንም በእሳት የሚቀርብ ቁርባን አድርጋችሁ በመሠዊያው ላይ ለጌታ አትሠዉ።
ስእለታችሁን ለመፈጸም፥ ወይም በፈቃዳችሁ፥ ወይም በበዓላችሁ፥ ለጌታ መዓዛው ያማረ ሽታ እንዲሆን ከበሬ ወይም ከበግ መንጋ የሚቃጠል መሥዋዕት ወይም መሥዋዕት የሚሆን በእሳት የሚቀርብ ቁርባን አድርጋችሁ ለጌታ ብታቀርቡ፥