ዘሌዋውያን 22:12 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የካህንም ልጅ ምእመንን ብታገባ፥ እርሷ ከተቀደሰው ቁርባን አትብላ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም የካህን ልጅ፣ ካህን ያልሆነ ሌላ ሰው ካገባች፣ ከተቀደሰው መሥዋዕት መብላት አትችልም። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ካህን ያልሆነ የውጪ ሰው ያገባች የካህኑ ልጅ ከተቀደሰው ስጦታ አትብላ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የካህንም ልጅ ከሌላ ወገን ጋር ብትጋባ፥ እርስዋ ከተቀደሰው ዐሥራት አትብላ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የካህንም ልጅ ከልዩ ሰው ጋር ብትጋባ፥ እርስዋ ከተቀደሰው ቍርባን አትብላ። |
የካህን ልጅ ግን ባልዋ ቢሞት፥ ወይም ብትፋታ፥ ልጅም ባይኖራት፥ በብላቴንነትዋ እንደ ነበረች ወደ አባትዋ ቤት ብትመለስ፥ ከአባትዋ እንጀራ ትብላ፤ ማናቸውም ምእመን ግን ከእርሱ አይብላ።