ዘሌዋውያን 21:21 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ከካህኑ ከአሮን ዘር ነውር ያለበት ማናቸውም ሰው ለጌታ በእሳት የሚቀርበውን ቁርባን ለማቅረብ አይቅረብ፤ ነውረኛ ነውና የአምላኩን እንጀራ ለማቅረብ አይቅረብ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከካህኑ ከአሮን ዘር ማንኛውም ዐይነት የአካል ጕድለት ያለበት ሰው ለእግዚአብሔር በእሳት የሚቀርብ መሥዋዕት ሊያቀርብ አይምጣ፤ እንከን ያለበት ስለ ሆነ፣ የአምላኩን ምግብ ለማቅረብ አይምጣ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በአጠቃላይ ከካህኑ አሮን ዘሮች መካከል የአካል ጒድለት ያለበት ማንም ሰው የሚቃጠል መሥዋዕት ወይም የምግብ ቊርባን ለአምላኩ ማቅረብ አይችልም። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ከካህኑ ከአሮን ዘር ነውር ያለበት ሰው የእግዚአብሔርን መሥዋዕት ያቀርብ ዘንድ አይቅረብ፤ ነውረኛ ነው፤ የአምላኩን መባ ያቀርብ ዘንድ አይቅረብ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ከካህኑ ከአሮን ዘር ነውር ያለበት ሰው የእግዚአብሔርን የእሳት ቍርባን ያቀርብ ዘንድ አይቅረብ፤ ነውረኛ ነው፤ የአምላኩን እንጀራ ያቀርብ ዘንድ አይቅረብ። |
ለአምላካቸው የተቀደሱ ይሆናሉ፥ የአምላካቸውንም ስም አያረክሱም፤ እነርሱም የአምላካቸው እንጀራ የሆነውን፥ ለጌታ በእሳት የሚቀርበውን ቁርባን ያቀርባሉና የተቀደሱ ይሆናሉ።