ዘሌዋውያን 20:20 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ሰውም ከአጎቱ ሚስት ጋር ቢተኛ፥ የአጎቱን ኃፍረተ ሥጋ ገልጦአል፤ ኃጢአታቸውን ይሸከማሉ፤ ያለ ልጅ ይሞታሉ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም “ ‘ማንኛውም ሰው ከአጎቱ ሚስት ጋራ ግብረ ሥጋ ቢፈጽም፣ አጎቱን አዋርዷልና ሁለቱም ይጠየቁበታል፤ ያለ ልጅም ይሞታሉ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም አንድ ሰው ከአጐቱ ሚስት ጋር ቢተኛ አጐቱን ያዋረደ ስለ ሆነ እርሱም ሆነ ሴትዮዋ ፍዳቸውን ይቀበላሉ፤ ያለ ልጅም ይቀራሉ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ሰውም ከቅርብ ዘመዱ ሚስት ጋር ቢተኛ የቅርብ ዘመዱን ኀፍረተ ሥጋ ገልጦአል፤ ያለ ልጅ ይሞታሉ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ሰውም ከአጎቱ ሚስት ጋር ቢተኛ፥ የአጎቱን ኃፍረተ ሥጋ ገልጦአል፤ ኃጢአታቸውን ይሸከማሉ፤ ያለ ልጅ ይሞታሉ። |
ጌታ እንዲህ ይላል፦ “ከዚህ ሰው ዘር የሚከናወንለት የለም፥ በዳዊትም ዙፋን ላይ የሚቀመጥ በይሁዳም የሚነግሥ ከእንግዲህ ወዲህ አይገኝምና፦ መካን በዘመኑም የማይከናወንለት ሰው ብላችሁ ጻፉ።”