La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




ዘሌዋውያን 20:16 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

አንዲት ሴት ወደ ማናቸውም እንስሳ ብትቀርብ፥ ከእርሱም ጋር ብትገናኝ፥ ሴቲቱንና እንስሳውን ግደል፤ ፈጽመው ይገደሉ፤ ደማቸው በራሳቸው ላይ ነው።

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

“ ‘አንዲት ሴት ወደ እንስሳ ቀርባ ግብረ ሥጋ ብትፈጽም፣ ሴቲቱንና እንስሳውን ግደሉ፤ ደማቸው በራሳቸው ላይ ነው።

Ver Capítulo

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

አንዲት ሴት ከእንስሳ ጋር ፍትወታዊ ግንኙነት ብታደርግ እርስዋም እንስሳውም ይገደሉ፤ ስለ መሞታቸውም ኀላፊነቱ የራሳቸው ይሆናል።

Ver Capítulo

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

ማን​ኛ​ዪ​ቱም ሴት ወደ እን​ስሳ ብት​ቀ​ርብ፥ ከእ​ር​ሱም ጋር ብት​ገ​ናኝ፥ ሴቲ​ቱ​ንና እን​ስ​ሳ​ውን ግደሉ፤ ፈጽ​መው ይገ​ደሉ፤ በደ​ለ​ኞች ናቸው።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

ማናቸይቱም ሴት ወደ እንስሳ ብትቀርብ፥ ከእነርሱም ጋር ብትገናኝ፥ ሴቲቱንና እንስሳውን ግደል፤ ፈጽመው ይገደሉ፤ ደማቸው በላያቸው ነው።

Ver Capítulo



ዘሌዋውያን 20:16
8 Referencias Cruzadas  

የማንም እጅ አይንካው፤ የሚነካው ግን በድንጋይ ይወገራል፥ ወይም በፍላጻ ይወጋል፤ እንስሳም ቢሆን፥ ሰውም ቢሆን አይድንም።’ ሳያቋርጥ የመለከት ድምፅ ሲነፋ በዚያን ጊዜ ወደ ተራራው ይውጡ።”


“በሬ ወንድን ወይም ሴትን እስኪሞቱ ድረስ ቢወጋ፥ በሬው ይወገር፥ ሥጋውም አይበላ፤ የበሬው ባለቤት ግን ንጹሕ ነው።


በሬው ወንድ ባርያ ወይም ሴት ባርያ ቢወጋ፥ የበሬው ባለቤት ሠላሳ የብር ሰቅል ለጌታው ይስጥ፥ በሬው ግን ይወገር።


ከጌታ በቀር ለሌላ አምላክ የሚሠዋ ፈጽሞ ይጥፋ።


በእርሱም ራስህን እንዳታረክስ ከማናቸውም እንሰሳ ጋር አትተኛ፤ ሴት ከእርሱ ጋር ለመተኛት በእንስሳ ፊት አትቁም፤ ጸያፍ የሆነ ተግባር ነው።


ማናቸውም ሰው ከእንስሳ ጋር ቢገናኝ ፈጽሞ ይገደል፤ እንስሳይቱንም ግደሉአት።


“ማናቸውም ሰው የአባቱን ልጅ ወይም የእናቱን ልጅ እኅቱን ቢያገባ፥ ኃፍረተ ሥጋዋንም ቢያይ፥ ኃፍረተ ሥጋውንም ብታይ፥ ይህ አሳፋሪ ነገር ነው፤ ከሕዝባቸውም ልጆች ፊት ተለይተው ይጥፉ፤ የእኅቱን ኃፍረተ ሥጋ ገልጦአልና በደሉን ይሸከማል።


ምክንያቱም “እንስሳ እንኳ ተራራውን ቢነካ ተወግሮ ይሙት፤” የምትለውን ትእዛዝ መሸከም አልቻሉም።