እርሷም አባትዋን፥ “ፊትህ ለመቆም ስላልቻልሁ አትቆጣብኝ፥ በሴቶች የሚደርስ ግዳጅ ደርሶብኛልና” አለችው። እርሱም ፈለገ፥ ነገር ግን ተራፊምን አላገኘም።
ዘሌዋውያን 19:32 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) “በአዛውንት ፊት ተነሣ፥ ሽማግሌውንም አክብር፥ አምላክህንም ፍራ፤ እኔ ጌታ ነኝ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም “ ‘ዕድሜው ለገፋ ተነሥለት፤ ሽማግሌውን አክብር፤ አምላክህንም ፍራ፤ እኔ እግዚአብሔር ነኝ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም “በዕድሜ የገፉ ሽማግሌዎች ሲመጡ ስታይ ከተቀመጥክበት በመነሣት አክብራቸው፤ እኔን አምላክህንም ፍራ፤ እኔ እግዚአብሔር ነኝ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) “በሽበታሙ ፊት ተነሣ፤ ሽማግሌውንም አክብር፤ አምላክህን እግዚአብሔርንም ፍራ፤ እኔ እግዚአብሔር አምላካችሁ ነኝና። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በሽበታሙ ፊት ተነሣ፥ ሽማግሌውንም አክብር፥ አምላክህንም ፍራ፤ እኔ እግዚአብሔር ነኝ። |
እርሷም አባትዋን፥ “ፊትህ ለመቆም ስላልቻልሁ አትቆጣብኝ፥ በሴቶች የሚደርስ ግዳጅ ደርሶብኛልና” አለችው። እርሱም ፈለገ፥ ነገር ግን ተራፊምን አላገኘም።
ስለዚህም ቤርሳቤህ የአዶንያስን ጉዳይ ልትነግር ወደ ንጉሡ ገባች፤ ንጉሡም ከተቀመጠበት ተነሥቶ እናቱን እጅ በመንሣት ተቀበላት፤ እርሱም በዙፋኑ ላይ ከተቀመጠ በኋላ ሌላ ዙፋን አስመጥቶ በቀኙ አስቀመጣት፤
በታላቅ ኃይልና በሥልጣን ከግብጽ ምድር ላወጣኋችሁ ለእኔ ለእግዚአብሔር ታዛዦች ሁኑ፤ መስገድና መሥዋዕት ማቅረብ የሚገባችሁ ለእኔ ብቻ ነው፤
የቡዛዊውም የባርክኤል ልጅ ኤሊሁ ተናገረ፤ እንዲህም አለ፦ “እኔ በዕድሜ ታናሽ ነኝ፥ እናንተ ግን ሽማግሌዎች ናችሁ፥ ስለዚህም ሰጋሁ፥ የማውቀውን እገልጥላችሁ ዘንድ ፈራሁ።